Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 27
Listen to find out how to ask about how much clothes cost.
አልባሳት ዋጋቸው ስንት እንደሆነ ለመጠየቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Session 27 score
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
How much is this?
Listen to find out how to ask about how much clothes cost.
አልባሳት ዋጋቸው ስንት እንደሆነ ለመጠየቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያንን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ዘሩባቤል እባላለሁ። በዚህ ክፍል ሱቅ ገብተው ዕቃ በሚገዙበት ጊዜ ዋጋ እንዴት እንደሚጠይቁ ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች ሱቅ ውስጥ ሲነጋገሩ ያዳምጡ።
Fiona
Hi, how much is this jacket?
Shop assistant
That jacket’s £59.99.
Fiona
Can I try it on?
Shop assistant
Of course you can.
ዘሩባቤል
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ ፊዮና ፊዮና ‘ይህ ጃኬት ዋጋው ስንት ነው?’ ‘How much is this jacket?’ ስትል ጠየቃለች። አንድን ነገር ብቻ በተመለከተ ስናወራ ‘this’ የሚለውን ቃል እንጠቀማለን። ከአንድ በላይ ስለሆኑ ነገሮች ስናወራ ግን ‘these’ የተባለውን ቃል እንጠቀማለን። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
Hi, how much is this jacket?
ዘሩባቤል
በመቀጠል የሱቁ ረዳት ‘That jacket is…’ ብሎ ዋጋውን በማስከተል መለሰ። ዋጋ የሚገለፀው ከነጥብ በፊት እና በኋላ ያሉትን አሃዞች አነጣጥሎ በመናገር ነው። ስለዚህም 59.99 ‘fifty-nine ninety-nine’ ሃምሳ ዘጠኝ ከዘጠና ዘጠኝ ይሆናል። 20.50 ‘twenty fifty’ ደግሞ ሃያ ከሃምሳ ይሆናልማለት ነው። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
That jacket’s £59.99.
ዘሩባቤል
በመቀጠል ፊዮና መሞከር እችላለሁ? ‘Can I try it on?’ ስትል ጠይቃለች። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Can I try it on?
ዘሩባቤል
በመጨረሻም የሱቁ ረዳት ‘በሚገባ፤ ትችያለሽ’ ‘Of course you can.’ ብሎ መልሷል። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Of course you can.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች ሱቅ ውስጥ ሲነጋገሩ በማዳመጥ ከእርሶ መልስ ጋር ያወዳድሩ።
Hi, how much is this sweater?
That sweater’s £24.99.
Can I try it on?
Of course you can.
Hi, how much is that coat?
This coat is £39.99.
Can I try it on?
Of course you can.
Hi, how much are these shorts?
Those shorts are £19.99.
Can I try them on?
Of course you can.
ዘሩባቤል
እሽ፥ ደግመን እንሞክር። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። አሁን እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጣሉ።
Hi, how much is this jacket?
Hi, how much is this jacket?
That jacket’s £59.99.
That jacket’s £59.99.
Can I try it on?
Can I try it on?
Of course you can.
Of course you can.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታውሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ጃኬቱ ስንት ነው?
Hi, how much is this jacket?
ጃኬቱ ሃምሳ ዘጠኝ ከዘጠና ዘጠኝ ነው።
That jacket’s £59.99.
መሞከር እችላለሁ?
Can I try it on?
በሚገባ
Of course you can.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሱቅ ውስጥ የአንድ ዕቃ ዋጋ ስንት እንደሆነ መጠየቅ ይችላሉ። ከሱቁ ረዳት ጋር ያለውን ውይይት ይለማመዱ። የሸሚዙን ዋጋ እና መሞከር ይችሉ እንደሆነ ይጠይቁ።
That shirt’s £19.99.
Of course you can.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን ጠቅላላውን ንግግር ደግመው ያዳምጡ እና መልስዎን ያመሳክሩ።
Fiona
Hi, how much is this jacket?
Shop assistant
That jacket’s £59.99.
Fiona
Can I try it on?
Shop assistant
Of course you can.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! አሁን ሸመታ ላይ ሲሆኑ የዕቃዎች ዋጋ ስንት አንደሆነ መጠየቅ ይችላሉ። የተማሩትን መለማመድ አይርሱ። ጓደኛ ይፈልጉና ‘How much is this?’ የሚለውን ጥያቄ በመጠየቅ ይለማመዱ። ለተጨማሪ የ Essential English Conversation ክፍሎች በሚቀጥለው ዝግጅታችን ይጠብቁን። Bye!
Check what you’ve learned by putting the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛው ቅደመ ተከተል በማስቀመጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
How much is this?
3 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
Help
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
Hint
ይህ ከአንድ በላይ የሆነን ነገር ዋጋ የምንጠይቀበት ጥያቄ ነው።Question 1 of 3
Help
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
Hint
ይህ አረፍተ ነገር የኮቱን ዋጋ ሊገልፅ ይገባዋል።Question 2 of 3
Help
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
Hint
ይህ ጥያቄ የአልባሳት መደብር ውስጥ አንድን ነገር ለመሞከር የሚቀርብ ነው።Question 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
Hi, how much is this ______?
ሃይ ይህ ______ ስንት ነው?
Hi, how much are these ______?
ሃይ እነዚህ ______ ስንት ናቸው?
jacket
ጃኬት
sweater
ሹራብ
coat
ኮት
shorts
ቁምጣ
That ______’s £______.
ያ ______ ዋጋው______ ፓውንድ ነው
Those ______ are £______.
እነዚህ ______ ዋጋቸው ______ ፓውንድ ነው
Can I try it on?
ልሞክረው እችላለሁ?
Can I try them on?
ልሞክራቸው እችላለሁ?
Of course, you can.
በሚገባ እንጅ፤ ትችላለህ።