Learning English

Inspiring language learning since 1943

English Change language

Session 8

Listen to find out how to talk about someone’s personality in English.
ስለአንድ ሰው ባህርይ በእንግሊዝኛ እንዴት ማውራት እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።

Sessions in this unit

Session 8 score

0 / 3

 • 0 / 3
  Activity 1

Activity 1

How do I talk about someone's personality?

ከማዳመጥዎ በፊት ከቃላት ሳጥኑ ውስጥ እነኝህን ቃላት ማወቅዎን ያረጋግጡ።

1. lazy
2. shy
3. quiet

የዛሬውን ክፍል ያዳምጡ እና ቀጥለው ያሉትን ጥያቄዎች ይመልሱ።

• Who in the family is lazy?
• Who in the family is quiet?
• Who in the family is shy?

መልሶችዎን ለማጣራት ማዳመጥዎን ይቀጥሉ። በመቀጠል ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያወዳድሩት።

Show transcript Hide transcript

ዘሩባቤል
ሰላም! እንኳን ወደ How do I… ዝግታችን በደህና መጡ፥ አቅራቢዎች እኔ ዘሩባቤል እና ፊል ነን።

Phil
Hello, everybody. Welcome!

ዘሩባቤል
በዛሬው ዝግጅታችን አንድ ሰው ምን እንደሚመስል መግለፅ ስለሚቻልባቸው ልዩ ልዩ መንገዶች እናወራለን። የተወሰኑ ሰዎች ስለሰዎች ባህሪ ሲነጋገሩ በማዳመጥ እንጀምር። ሰዎች የቤተሰብ አባሎቻቸውን ሲገለፁ ያዳምጡ። የትኞቹን የቤተሰብ ቃላት አዳመጡ?

What's your brother like?
He’s so friendly but he’s a little lazy.

What’s your mother like?
She’s funny, but a little shy.

What’s your father like?
He’s too serious and so quiet.

ዘሩባቤል
ምን አሰቡ? ስለሰዎች ባህሪ የሚገልፁ በርካታ ገላጭ ቃላት ነበሩ። በመጀመሪያ ግን ማንኛውም ትንሽዬ የንግግር ልውውጥ የሚጀመረው በተመሳሳይ ጥያቄ ሲሆን ያም ጥያቄ ‘what’s he or she like?’ ነው። ‘is like’ ስለሰዎች ባህርይ ለማውራት እና ለመጠየቅ እንጠቀምበታለን። ፊልን ያዳምጡና ጥያቄውን ይለማመዱ።

Phil
Listen carefully to the pronunciation of ‘what’s’. Listen and repeat.

What’s he like?

ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! የመጀመሪያው ሰው እንዴት እንደተገለፀ ያስታውሳሉ? ደግመን እናዳምጥ።

He’s so friendly but he’s a little lazy.

ዘሩባቤል
የሰውየውን ባህርይ ለመገልፅ ጥቅም ላይ የዋሉ ሁለት ቃላት ነበሩ። በመጀመሪያ ‘friendly’ ተጨዋች ወይንም ቅልል ያለ የሚለውን ሰምተናል። ከ ‘friendly’ በፊት የነበረውን ቃል ሰምተዋል? አዎ’፤ ‘so’ ነበር። ይሄንን ቃል የአንድ ሰው ባህርይ ላይ አፅንዖት ለመስጠት የምንጠቀምበት ቃል ነው። ሁለተኛው ገላጭ ቃል ምንድን ነበር?

Phil
It was ‘lazy’. Did you hear the word in front of this word?

ዘሩባቤል
‘A little’ ነበር። ይሄንን ቃል ብዙ ጊዜ አዎንታዊ ትርጉም ካላቸው ገላጭ ቃላት ጋር የምንጠቀመው ሲሆን፥ አንድ ሰው የተባለው ባህርይ በጥቂቱ ብቻ እንዳለው ለመግለፅ ያገለግለናል።

Phil
That’s right, so we can say ‘a little lazy’ and ‘a little silly’. Let’s practise saying that whole sentence. Listen and repeat.

He’s so friendly but he’s a little lazy.

ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! ቀጣዩ ንግግር በተመሳሳይ ጥያቄ ይጀምራል። ያዳምጡ።

What’s your mother like?

ዘሩባቤል
አሁን ሴትዮዋ እንዴት እንደተገለፀች እናዳምጥ።

She’s funny, but a little shy.

ዘሩባቤል
እዚህ ላይ የተለያዩ የሆኑ ሁለት ቃላት አሉን ‘funny’ እና ‘shy’ ፤ ስለዚህም ተቃራኒ የባህርይ ዓይነቶችን ለማያያዝ ይሄንን ልዩ ቃል ‘but’ እንጠቀማልን።

Phil
Yes, so I could say that you are ‘a little lazy, but so friendly’.

ዘሩባቤል
አመሰግናለሁ. . . መሰለኝ።

Phil
Let’s practise saying whole sentence. Repeat after me.

She’s funny, but a little shy.

ዘሩባቤል
የመጨረሻው ንግግር ተመሳሳዩን ጥያቄ ይጠይቃል። ምላሹ ይሄው።

He’s too serious and so quiet.

ዘሩባቤል
እዚህ ላይ ‘too’ የተባለው ቃል አለን። የሆነ ነገር የተጋነነ መሆኑን ለመግለጽ እንጠቀመዋለን። የአንድን ሰው ባህሪ አጉልቶ ለማውጣት ይጠቅማል።

Phil
So, I can say somebody is ‘too loud’, or ‘too old’.

ዘሩባቤል
አዎ። በመጨረሻ ሁለቱም ‘too serious’ እና ‘so quiet’ አሉታዊ ቃላት ናቸው፤ ተመሳሳይ ኃሳቦችን ለማያያዝ ‘and’ እንጠቀማለን።

Phil
That’s right. So we can say somebody is ‘too quiet and a little lazy’.

ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! ስለሰዎች ባህሪ የምናወራባቸውን የተለያዩ መንገዶችን ተምረዋል እና አሁን የመለማመጃ ሰዓት ነው። ወንድምዎት ምን ዓይነት ሰው እንደሆነ የሆነ ሰው እንደጠየቀዎት ያስቡ። ያዳምጡ።

What’s your brother like?

ዘሩባቤል
ወንድምዎት ደግ እና ለሰዎችም መልካም እንደሆነ ለመናገር ይሞክሩ።

Phil
He’s friendly.

ዘሩባቤል
ተመሳሳይ ነገር ነው ያሉት?
አንድ ሌላ እስቲ እንሞክር። አሁን ደግሞ ሰዎችን የሚያስቅ እንደሆነ አድርገው ይግለፁት።

Phil
He’s funny.

ዘሩባቤል
መልስዎት ከፊል ጋር አንድ ዓይነት ከሆነ በጣም ጥሩ። አሁን የመሰነባበቻ ሰዐት ላይ ደርስናል። በዛሬው ዕለት የተማሩትን ከጓደኞችዎ ጋር መለማመድ አይዘንጉ፤ ለሰዎች ባህሪ አፅንዖት ለመስጠት ‘too’ ፥ ‘so’ እና ‘a little’ መጠቀሞንም አይርሱ።

Phil
Good idea! Goodbye everyone!

ዘሩባቤል
Goodbye!

Learn more! 

1. ‘Be like’ ምን ማለት ነው?

ይሄንን ቅርፅ ስለሰዎች ባህሪ ለመጠየቅ እንጠቀምበታለን። ጥያቄው ቀጥሎ አለ።

• What’s he like?
• What’s she like?

2. ‘So’ ፥ ‘too’ እና ‘a little’ እንዴት መጠቀም እችላለሁ?

አንድ ባህርይ ላይ አፅንዖት ለመስጠት ‘so’ እንጠቀማለን። ‘very’ ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ትርጉም ነው ያለው።

• He is so kind.

‘Too’ የምንጠቀመው አንድ ሰው በዛ ያለ ባህርይ እንዳለው ለመገልፅ ነው። ‘too’ ከተጠቀምን ብዙ ጊዜ ትችት ወይንም አሉታዊ ፍርድ ነው።

• She is too lazy.

አንድ ሰው አንድ ባህርይ በጥቂቱ እንዳለው ለመግለፅ ‘a little’ እንጠቀማለን።

• He is a little shy.

3.‘But’ እና ‘and’ በአረፍተ ነገር ውስጥ እንዴት መጠቀም እንችላለን?

‘But’ የምንጠቀመው ሁለት ተቃራኒ ኃሳቦችን ለማያያዝ ሲሆን and’ ደግሞ ተመሳሳይ ቃላትን ለማያያዝ እንጠቀመዋለን።

• He’s so friendly, but a little quiet.
• She’s so kind and funny.

ስለ አንድ ሰው ባህሪ እንዴት ነው የማወራው?

3 Questions

Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።

Congratulations you completed the Quiz
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
x / y

Can you describe the personality of somebody you know in English? Tell us on our Facebook group!
የአንድን ሰው ባህሪ በእንግሊዝኛ መግለጽ ይችላሉ? በፌስቡክ ቡድናችን ይሄንን ይንገሩን።

Join us for our next episode of How do I… when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ጠቃሚ ቋንቋዎችን ለመማርና የማዳመጥ ክህሎትዎን በልምምድ ለማዳበር ቀጣዩን How do I… ዝግጅታችንን ይከታተሉ።

Session Vocabulary

 • What’s he/ she like?
  ምን ዓይነት ሰው ነው/ናት?

  too
  በጣም

  so
  በጣም

  a little
  በጥቂቱ

  but
  ነገር ግን

  and
  እና

  friendly
  ተግባቢ

  lazy
  ሰነፍ

  funny
  ቀላጅ/አስቂኝ

  shy
  ዓይናፋር

  serious
  ኮስታራ

  quiet
  በጥቂቱ

  talkative
  ወሬኛ

  hardworking
  ታታሪ