Unit 1: How do I...
Select a unit
- 1 How do I...
- 2 Unit 2
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 7
Listen to find out how to talk about someone’s appearance in English.
በእንግሊዝኛ ስለአንድ ሰው የውጭ ገፅታ እንዴት ማውራት እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Activity 1
How do I talk about someone's appearance?
የምናውቃቸውን ሰዎች ውጫዊ ገፅታ ስናብራራ ጥሩ የሚባል ዝርዝር መረጃ እንዴት መስጠት እንችላለን?
ይሄንን ለማወቅ የዛሬውን ክፍል ያዳምጡ።
መልሶችዎን ለማጣራት ማዳመጥዎን ይቀጥሉ። በመቀጠል ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያወዳድሩት።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ወደ How do I… ዝግጅታችን በደህና መጡ። አሰተናጋጃችሁ እኔ ዘሩባቤል ነኝ…
Tom
And, hi everybody! I’m Tom, welcome to today’s episode of How do I…!
ዘሩባቤል
በዚህ ዝግጅት የአንድ ሰው አካላዊ ገፅታ ምን እንደሚመስል የምንገልፅባችው ልዩ ልዩ መንገዶችን እንመለከታለን። ሁለቱ ተናጋሪዎች ሰዎችን እየገለፁ ነው፤ ሰዎቹም ‘mother’ እናት እና የወንድ ጓደኛ ‘boyfriend’ ናቸው። ያዳምጡና ጥያቄውን ይመልሱ፤ ‘blonde hair’ ወርቃማ ፀጉር ያለው የትኛው ሰው ነው?
What does your boyfriend look like?
He's tall and has short, blonde hair.
What does your mother look like?
She's quite short and has long, dark hair.
ዘሩባቤል
አዳመጣችሁ? የመጀመሪያዋ ተናጋሪ የወንድ ጓደኛ ‘short, blonde hair’ አለው።
Tom
So, let’s begin today’s lesson on appearance!
ዘሩባቤል
እሽ፤ ‘look like’ እዚህ ላይ ያሉት ወሳኝ ሁለት ቃላት ናቸው። ስለ አንድ ሰው አካላዊ ገጽታ ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን።
ተናጋሪዎቹ ስለሰዎች አካላዊ ገፅታ ለመጠየቅ ምን አሉ? የተጠቀሙት ‘do’ ወይንስ ‘does’ ነው?
Tom
Let’s listen again to find out!
What does your boyfriend look like?
What does your mother look like?
ዘሩባቤል
አዳመጣችሁት? የ ‘do’ የሶስተኛ መደብ ቅርፅ የሆነውን ‘does’ ተጠቅመዋል። በጥያቄ ቅርፅ ሲሆን ሁሌም ከ ‘he’፥ ‘she’ ወይንም ‘it’ ጋር ‘does’ አንጠቀማለን። ቶም እባክህን የጥያቄውን አነባበብ ማሳየት ትችላለህ?
Tom
Of course!
Let’s work backwards to help with our rhythm. Repeat after me:
…does your…
What does your…
Now let’s make it complete! Let’s add ‘mother’ and ‘look like’. ‘Mother’ and ‘look’ have strong stress.
What does your mother look like?
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! ብዙም ሳይቆይ ጥሩ ተናጋሪ ይሆናሉ! ለጥያቄው መልስ ለመስጠት የ ‘be’ እና ‘have’ ቅርፆች እንጠቀማለን። የትኛውን የ ‘be’ ቅርፅ ነው የተጠቀሙት?
He's tall and has short, blonde hair.
She's quite short and has long, dark hair.
Tom
They say ‘he’s’ or ‘she’s’. The speakers are using the short form of ‘is’.
ዘሩባቤል
እዚህ ላይ ‘is’ የሆነውን የ ‘be’ ቅርፅ ከተጠቀሙ በኋላ ተናጋሪዎቹ እየገለጹት የነበረውን ሰው መጠን ገለፀዋል። ስለሰዎች ዕድሜ፥ አካላዊ ቅርፅ ለመናገር እንዲሁም ስለሰዎች ያለንን አመለካከት ለመገልፅም እንጠቀምበታለን።
Tom
The first speaker says ‘he’s tall’. The second speaker says ‘she’s quite short’.
ዘሩባቤል
ትክክል ነው። ‘Tall’ የ ‘short’ ተቃራኒ ነው። ‘Quite’ ማለት ‘not very’ እንደ ማለት ነው። ‘Quite short’ ስንል ‘short’ የተባለውን ቃል ጥንካሬ እናሳንሰዋለን።
That’s not all! የፀጉርን ርዝመት እና ቀለም ለመግለፅ ‘have’ እንጠቀማለን። የዓይን ቀለምን የመሳሰሉ የፊት ገፅታዎችንም ይገልፃል።
ተናጋሪዎቹ የወንድ ጓደኛቸው እና እናታቸው ‘have’ ምን እንዳላቸው የተናገሩት ምን ነበር? እናዳምጥ።
He's tall and has short, blonde hair.
She's quite short and has long, dark hair.
ዘሩባቤል
እዚህ ላይ ‘have’ ስለፀጉር ለማውራት ተጠቅመንበታል። ‘Has’ የ ‘have’ ሶስተኛ መደብ ቅርፅ ሲሆን ከ ‘he’፥‘she’ ወይንም ‘it’ ጋር እንጥቀመዋለን። ልብ ይበሉ! ‘A’ ከ ‘hair’ ጋር አንጠቀመውም። እርሱን ማድረግ ስለአንድ ነጠላ ፀጉር ማውራት ይሆንብናል።
Tom
OK! Now, time to practise!
ዘሩባቤል
በመጀመሪያ ይችን በጣም የተደሰተች ሴት ያዳምጡ። ስለምንድን ነው የምታወራው?
Hey! I’m so happy! I have a new boyfriend!
ዘሩባቤል
ይገርማል! የወንድ ጓደኛ! ‘የወንድ ጓደኛሽ ምን ይመስላል?’ ብለው የሚጠይቁት እንዴት ነው?
Tom
What does your boyfriend look like? You could also say ‘what does he look like’?
ዘሩባቤል
ተመሳሳይ ነገር ነው ያሉት?
አሁን እርስዎም ለጥያቄው መልስ ለመስጠት ይሞክሩ።
What does your best friend look like?
ዘሩባቤል
‘በመጠኑ አጭር ስትሆን ረጅም ፀጉር አላት’ ይበሉ።
Tom
She’s quite short and has long hair.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! ያስታውሱ ‘quite’ በጥቂቱ ማለት ነው።
Tom
Great! So, now you know how to describe appearance, practise with some of your friends!
ዘሩባቤል
ለሌላ ድንቅ የ How do I… ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት መከታተልዎን አይዘንጉ። Bye!
Tom
Bye, everyone! See you next time.
Learn more!
1. ስለአንድ ሰው ውጫዊ ገፅታ እንዴት መጠየቅ እችላለሁ?
ስለአንድ ሰው ውጫዊ ገፅታ ስንጠይቅ አብዩ ግስ 'look' መምሰል ነው፤ መምሰል ከሌላ አንድ ቃል አንድ ላይ በመሆን 'look like' የተባለውን ሐረግ ይፈጥራል።
'Do' የጥያቄ ቅርፅ እንድንመሰርት የሚያግዘን ረዳት ግስ ነው። ስለ 'he' ወይንም ስለ 'she' ስንጠይቅ 'does' የተባለውን ቅርፅ እንጠቀማለን፤ የቃላቱ ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፡
What does he/ she look like?
2. ስለአንድ ሰው ውጫዊ ገፅታ እንዴት መጠየቅ እችላለሁ?
'Be' የአንድን ሰው ውጫዊ ገፅታ ለመገለፅ የምንጠቀምበት ቃል ነው፤ 'is' የ 'be' ሦስተኛ መደብ ነው። 'Be' ስለአንድ ሰው ቁመት ለማውራት ልንጠቀምበት እንችላለን። 'Tall' እና 'short' ቁመትን ለመግለፅ አዘውትረው ግልጋሎት የሚሰጡ ገላጭ ቃላት ናቸው።
He is tall.
'Be' ስለአንድ ሰው ዕድሜ እና የአካል ግንባታ እንዲሁም ስለአንድ ሰው ያለንን አመለካከት ለመግለፅ እንጠቀምበታለን። ይሄንን ለመግለፅ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ቅፅሎች 'pretty' ቆንጆ (ለሴት) እና 'handsome' መልከ መልካም (ለወንድ) ናቸው።
She is 25 years old.
She is pretty.
He is tall and thin.
አንዳንድ ጊዜ 'quite' የተባለውን ገላጭ ግስ እንጠቀማለን። 'Quite' የቅፅልን ወይንም የገላጭን ጥንካሬ ለመቀነስ የምንጠቀምበት ቃል ነው፤ በመጠኑ የማለት ያህል ነው።
She is quite short.
He is quite tall.
3. አንድን ሰው ለመግልፅ 'have' መጠቀም እችላለሁ?
'Have' የፀጉር ርዝመት እና ቀለም እንዲሁም የዓይን ቀለምን የመሳሰሉ የፊት ግፅታዎችን ለመግልፅ እንጠቀምበታለን። የ 'have' ሦስተኛ መደብ ቅርፅ 'has' ነው።
He has short, blonde hair.
She has big blue eyes.
'A' ከ 'hair' ጋር እንደማንጠቀመው ልብ ይበሉ። እርሱን ማድረግ ስለአንድ ነጠላ ፀጉር ማውራት ይሆንብናል። ከዚህም ባሻገር ከፀጉር ቀለም በፊት ርዝመትን መግለፅ ይኖርብናል።
ስለአንድ ሰው ውጫዊ ገፅታ እንዴት መጠየቅ እችላለሁ?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
ሁለት ቃላትን መጠቀም ይኖርብናል።Question 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
እዚህ ላይ የአረፍተ ነገሩ ባለቤት she ነው፤ ስለዚህም ግሱ ከመሰረታዊ ቅርፁ ይቀየራል።Question 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
ያስታውሱ፤ ከፀጉር ቀለም በፊት ስለርዝማኔው እናወራለን።Question 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Can you describe the appearance of somebody you know in English? Tell us on our Facebook group!
አንድ የሚያውቁትን ሰው ውጫዊ ገፅታ በእንግሊዝኛ መግለፅ ይችላሉ? በፌስቡክ ቡድናችን ይሄንን ይንገሩን።
Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ጠቃሚ ቋንቋዎችን ለመማርና የማዳመጥ ክህሎትዎን በልምምድ ለማዳበር ቀጣዩን How do I… ዝግጅታችንን ይከታተሉ።
Session Vocabulary
mother
እናት
boyfriend
የወንድ ጓደኛ
pretty
ቆንጆ (ለሴት)
handsome
መልከ መልካም (ለወንድ)
long
ረጅም
short
አጭር
blonde
ባለወርቅማ ፀጉር
dark
ጥቁር
blue
ሰማያዊ
tall
ረጅም