Unit 1: How do I...
Select a unit
- 1 How do I...
- 2 Unit 2
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 17
Listen to find out how to talk about future arrangements.
ስለወደፊት ውጥኖች እንዴት እንደምንናገር ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Activity 1
How do I talk about future arrangements?
ከሚከተሉት አረፍተ ነገሮች መካከል ስለወደፊት ውጥን የሚያወራው የቱ ነው?
I'll have dinner with my mother tomorrow.
I'm having dinner with my mother tomorrow.
I had dinner with my mother yesterday.
መልስዎን ለመፈተሽ ማዳመጥዎን ይቀጥሉ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያመሳክሩ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ወደ 'How do I…' ዝግጅታችን በሰላም መጡ። አስተናጋጃችሁ እኔ ምህረተስላሴና ፊል አብረናችሁ ነን።
Phil
Hello, everybody. Welcome!
ምህረተስላሴ
በዚህ ክፍል እንዴት ስለወደፊት ውጥኖች ማውራት እንደምንችል እንማራለን። አንድ ሰው የሶስት ግለሰቦችን እቅድ ሲጠይቃቸው በማዳመጥ እንጀምር። ንግግራቸው ባይገባዎት ብዙም አይጨነቁ፤ ኋላ እናግዝዎታለን። ለአሁኑ ከተናጋሪዎቹ መካከል ምንም ሳይደርግ የሚውለው ማን እንደሆነ ለመረዳት ይሞክሩ።
What are you doing tomorrow?
I'm having lunch with my mother.
I'm going to work, as usual.
I'm not doing anything. It's my day off.
ምህረተስላሴ
አዳመጡ? የመጨረሻው ሰው ምንም ነገር አያደርጉም፤ በነጋታው ሰከን ያለ ቀን ያሳልፋሉ። ስለዚህ ፊል ስለወደፊት ውጥን ለማውራት የምንጠቀምበትን ቋንቋ እንመልከት?
Phil
Yes, let's have a look!
ምህረተስላሴ
በአረፍተ ነገሮቹ ባጠቃላይ ሰዎች ስለወደፊት እቅዳቸው ያወራሉ። ምን ዓይነት አረፍተ ነገር ነው የተጠቀሙት? ጥያቄውን በድጋሚ እናዳምጥ።
What are you doing tomorrow?
ምህረተስላሴ
የተጠቀሙት አሁን ላይ ያለማቋረጥ እየተደረገ ያለ ተግባርን የሚገልጽ 'what are you doing?' የተሰኘ አረፍተ ነገር ነው። ይህንን አረፍተ ነገር በቀጣይ ልናደርግ ስለወጠናቸው ነገሮች ለመግለጽ እንጠቀምበታለን።
Phil
OK, let's quickly practise the pronunciation together! Notice that when we say "What are you doing tomorrow" we pronounce 'are' as 'uh' 'What are you doing tomorrow?' Repeat after me:
What are
What are you
What are you doing tomorrow?
What are you doing tomorrow?
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ። ለመጀመሪያው ጥያቄ የተሰጠውን መልስ እናዳምጥ።
I'm having lunch with my mother.
ምህረተስላሴ
ስለዚህም የ 'to be' ግሶችን ከ 'ing' ጋር እንጠቀማለን። በዚህ አረፍተ ነገር የተጠቀምነው 'am' የሚለውን ነው። ዋናው ግስ 'have' ወደ 'having' ይቀየራል ማለት ነው።
Phil
OK, Let's practise the pronunciation again. Notice how we say 'I am' as 'I'm'. Repeat after me:
I'm
I'm having
I'm having lunch with my mother.
I'm having lunch with my mother.
ምህረተስላሴ
አስከትለን፤ ቀጣዩን ሰው እናዳምጥ።
I'm going to work, as usual.
ምህረተስላሴ
እሺ፤ በድጋሚ 'I'm' ነው ያለው። ዋናው ግስ ደግሞ 'going' ነው። ከዚህም በተጨማሪም ግለሰቡ 'as usual’ የሚለውን ተጠቅሟል። ይህም አዘውትረው የሚያደርጉት ነገር ነው ማለት ነው።
Phil
And let's practise the pronunciation together. Notice how 'to' in 'going to work' sounds like 'tuh'. Repeat after me:
I'm going
I'm going to
I'm going to work as usual.
I'm going to work as usual.
ምህረተስላሴ
አንድ ተጨማሪ ነገር አለን። ይህ የመጨረሻው ሰው የወጠነው ነገር ምንድን ነው?
I'm not doing anything. It's my day off.
ምህረተስላሴ
ምንም አላደርግም 'not doing anything' ነው ያሉት። አሉታዊ አረፍተ ነገር ለመመሥረት 'not' ን እንጨምራለን። እዚያ ላይ ደስ የሚል 'it's my day off' የተባለ አገላለፅን ጨምረውም ተጠቅመዋል። አገላለጹ በእለቱ ምንም እንደማይሰሩ ያመለክታል።
Phil
When you can say 'I'm not doing anything' remember that it's important to stress the 'not'. Repeat after me:
I'm
I'm not
I'm not doing anything.
I'm not doing anything.
ምህረተስላሴ
ስለወደፊት ውጥኖች ለማውራት የምንጠቀምበት ቋንቋ ተምረዋል። አሁን መለማመጃ ሰአት ላይ እንገኛለን።
ሲኒማ ቤት ሄደው ፊልም ለማየት አቅደዋል እንበል። እንዴት ይገልጹታል? ለንፅፅር የፊልን መልስ ያዳምጡ።
Phil
I'm seeing a film at the cinema.
ምህረተስላሴ
'I'm going to see a new film' ማለትም ይችላሉ። አሁን አንድ የሚያውቁትን ሰው ለዛሬ ምሽት 'this evening' አንዳች ዕቅድ እንዳላቸው ለመጠየቅ አስበዋል እንበል። ምን ይላሉ? 'do' የተባለውን ግስ ይጠቀሙ። ሲጨረሱ ለንፅፅር የፊልን መልስ ያዳምጣሉ።
Phil
Are you doing anything this evening?
ምህረተስላሴ
Did you say the same?
Phil
Well done! Now you know how to talk about future arrangements!
ምህረተስላሴ
Great! Are you practising English this week? Bye!
Phil
Bye!
Learn more!
1. ስለወደፊት ውጥን ለማውራት የምጠቀምበት የአረፍተ ነገር መዋቅር የቱ ነው?
ለዚህ የምንጠቀመው ቀጣይነት ያለው የአረፍተ ነገር ዓይነት ነው። የአሁን ጊዜ ቀጣይነት ያለውን የአረፍተ ነገር ዓይነት ውጥኑ እንደሚከናወን እርግጠኛ ከሆንን ወይንም ካመቻቸን መጠቀም እንችላለን።
2. እንዴት ነው የምንመሰርተው?
አዎንታዊው
I'm having dinner with my mother. > ባለቤት + የ ‘be’ ግስ የአሁን ቅርፅ + ግስ + ‘ing’
አሉታዊው ቅርፅ
I'm not having dinner with my mother. > ባለቤት+ የ ‘be’ ግስ የአሁን ቅርፅ + ኖት + ግስ + ‘ing’
ጥያቄው
Are you having dinner with your mother? > የ ‘Be’ ግስ የአሁን ቅርፅ + ባለቤት+ ግስ + ‘ing’
የማሳጠሪያ ቅርፆችን ልብ ይበሉ
'I am' የሚለው I'm ይሆናል
'You are' የሚለው 'You're ይሆናል
'He is' የሚለው He's ይሆናል
'We are' የሚለው We're ይሆናል
3. የአሁን ጊዜ ቀጣይነት ያለው አረፍተ ነገር ሌሎች ጥቅሞች አሉት?
Yes, አዎ፤ የአሁን ጊዜ ቀጣይነት ያለው አረፍተ ነገር ሌሎችም ጥቅሞች ስላሉት ይጠንቀቁ። ከሌሎቹ ጥቅሞቹ መካከል አሁን በመካሄድ ላይ ያለን ነገር መግለፅ አንዱ ነው። የትኛውን የጊዜ ክልል በተመለከተ እያወራን እንደሆነ ከአገባብ ጠቋሚዎች ወይንም ከጊዜ ጠቋሚዎች በመነሳት እናውቃለን።
I'm having dinner with my mother at the moment.
I'm having dinner with my mother tomorrow.
How do I talk about future arrangements?
5 Questions
Choose the correct answer
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Help
Activity
Choose the correct answer
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
ለውጥኖች/ዕቅዶች የምንጠቀምበት የአረፈተ ነገር ዓይነት ምንድን ነው?Question 1 of 5
Help
Activity
Choose the correct answer
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
ዕቅዱን ለመከወን ሁኔታዎችን ተመቻችተዋል።Question 2 of 5
Help
Activity
Choose the correct answer
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
የአሁን ጊዜን ቀጣይነት ያለው አረፍተ ነገር የምንመሰርተው እንዴት ነው?Question 3 of 5
Help
Activity
Choose the correct answer
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
አሉታዊ የአሁን ጊዜ ቀጣይነት ያለው አረፈተ ነገርን ለመመስረት የምንጠቀምበት ቃል ምንድን ነው?Question 4 of 5
Help
Activity
Choose the correct answer
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
የአሁን ጊዜ ቀጣይነት ያለው ጥያቄን መመስረት የምንችለው እንዴት ነው?Question 5 of 5
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Tell us what you are doing this week on our Facebook group!
በዚህ ሳምንት ምን እንደሚያደርጉ በፌስቡክ ቡድናችን ይግለፁልን።
Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ ቋንቋ የምንማርበት እና የማዳመጥ ክህሎትዎን የሚያዳብሩበት How do I… ዝግጅቶችን ለማዳመጥ በቀጣዩ ክፍል ይጠብቁን።
Session Vocabulary
as usual
እንደሁሌውday off
የእረፍት ቀንlisten to music
ሙዚቃ ማዳመጥcinema
ሲኒማ