Learning English

Inspiring language learning since 1943

English Change language

Session 16

Listen to find out how to talk about your childhood hobbies.
ስለልጅነት መዝናኛዎችዎች እንዴት ማውራት እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።

Sessions in this unit

Session 16 score

0 / 4

 • 0 / 4
  Activity 1

Activity 1

How do I talk about my childhood hobbies?

ከእነዚህ አረፍተ ነገሮች መካከል ስለልማድ የሚያወራው የትኛው ነው?

I played football last week.
I was playing football yesterday afternoon.
I used to play football as a child.

መልስዎን ለማመሳከር ማዳመጥዎን ይቀጥሉ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያነፃፅሩት።

Show transcript Hide transcript

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ወደ How do I… ዝግጅታችን በደህና መጡ። አብረናችሁ አስተናጋጃችሁ እኔ ምህረተስላሴና ሳም አለን።

Sam
Hello, everybody. Welcome!

ምህረተስላሴ
በዚህ ክፍል የምናወራው. . . ቆይ እስኪ መገመት ይችሉ እንደሆን እንይ። በመጀመሪያ የተለያዩ ሰዎች ስለትርፍ ጊዜ መዝናኛዎቻቸው ሲያወሩ እናዳምጥ። ሰዎቹ የሚናገሩት ሰለሚያዘወትሯቸው መዝናኛዎች፣ ማድረግ ስለሚፈልጉት ነገር ወይስ በልጅነታቸው ስለነበሯቸው መዝናኛዎች ነው?

A.I used to play football with my friends but now I don’t.
B.I used to watch a lot of films when I was a child.
C.I didn’t use to listen to music much when I was young.

ምህረተስላሴ
ታዲያ ያዳመጣችኋቸው ሰዎች ያወሩት አሁን ስላሏቸው ፍላጎቶች ወይም መዝናኛዎች ነው? ወይንስ ከዚህ ቀደም ስለነበሯቸው?

Sam
Absolutely! Now let’s have a look at the language they used.

ምህረተስላሴ
ሰዎቹ በንግግራቸው የገለጹት ስላለፉ ልማዶቻቸው ‘past habits’ ነው፤ እነዚህ በቀደመው ጊዜ በተደጋጋሚ ያደርጓቸው የነበሩ ተግባሮች ናቸው። ይሄንን ለመግለጽ የተጠቀሙበት ሐረግ ምንድን ነው? በድጋሚ እናዳምጥ።

I used to play football with my friends.
I used to watch a lot of films.

ምህረተስላሴ
ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ይከናወን የነበረ ድርጊትን ለመግለፅ የምንጠቀምበት ሐረግ ‘used to’ ነው።

Sam
Yes, and did you hear what we put after ‘used to’?

ምህረተስላሴ
አሁን ደግሞ ከ ‘used to’ በኋላ ምን እንዳስገባን ልብ ብለን እናዳምጥ።

I used to play football with my friends.
I used to watch a lot of films.

ምህረተስላሴ
እያንዳንዱ ተናጋሪ ከ ‘used to’ በኃላ ግስ ወይም ድርጊት ገላጭ ቃል አስከትሏል። ‘play’ መጨዎት፣ ‘watch’ መመልከት የሚሉትን ግሶች ተጠቅመናል፤ ይሁን እንጂ ማንኛውንም ግስ መጠቀም እንችላለን።

Sam
Now, let’s quickly practise the pronunciation together! The important thing to notice here is that we pronounce ‘used to’ together, not like it’s two separate words. Repeat after me:
used to…
I used to…
I used to play football.
I used to watch films.

ምህረተስላሴ
ግሩም፤ አንድ ተናጋሪ ለየት ያለ አገላለጽ ተጠቅሟል። አሉታዊ ቃላት በመጠቀም ያላደረገውን ነገር ተናግሯል። የተናገረውን ለመረዳት የተጠቀመውን ቃላት ልብ ብለን እናዳምጥ።

I didn’t use to listen to music much.

ምህረተስላሴ
አዳመጣችሁት? ከ ‘use to’ በፊት ‘didn’t’ ተጠቅሟል። ከዚያም ‘didn’t’ በኋላ እንደቀደመው ጊዜ ሁሉ ግስን አስከትሏል።

Sam
Yes, it is! Let’s practise the pronunciation together. Repeat after me:
didn’t…
didn’t use to…
I didn’t use to...
I didn’t use to listen to music much.
I didn’t use to play football.

ምህረተስላሴ
ስላለፉ ጊዜ ልማዶች እንዴት መናገር እንደሚቻል ተምረዋል። አሁን ልምምድ ማድረጊያ ጊዜ ላይ ደርሰናል።
ልጅ ሳሉ ብዙ ፊልም እንደማያዩ ያስቡ። የሚያስፈልግዎት ቃላት ‘watch films’ ናቸው፤ አሉታዊ አገላለጽ መጠቀም እንዳለብዎት ያስታውሱ። ለንፅፅር የሳምን መልስ ይሰማሉ።

Sam
I didn’t use to watch films.

ምህረተስላሴ
Did you say the same as Sam?
አሁን ደግሞ በልጅነትዎ ሙዚቃ የማዳመጥ ልማድ ነበረዎት እንበል። እንዴት ይገልጹታል? ‘Listen to music’ የሚሉትን ቃላት መጠቀም ያስታውሱ፤ ለንፅፅር የሳምን ምላሽ ያዳምጣሉ።

Sam
I used to listen to music.

ምህረተስላሴ
Did you say the same?
በመጨረሻ የልጅነት ልማድዎ እግር ኳስ መጫዎት እንደነበር ያስቡ። ይሄንን እንዴት ይናገሩታል? ‘play football’ የተባሉትን ቃላት መጠቀምን ያስታውሱ። ከዚያም መልስዎን ያነፃፅሩ።

Sam
I used to play football.

Well done! Now you know how to talk about past habits, so find a friend and tell them about your childhood hobbies!

ምህረተስላሴ
Good idea! Sam, what were your childhood hobbies?

Sam
Well, I used to play the piano…I used to read a lot… I didn’t use to watch much television…

Learn more! 

1. ስላለፈው ጊዜ ለማውራት መጠቀም ያለብኝ ‘used to’ ን ብቻ ነው?

Yes! አዎ። እዚህ ላይ ባለፈው ጊዜ ከአንድ ጊዜ በላይ ስለደጋገምናቸው ልማዶች፣ የዘወትር ተግባሮች ወይንም ድርጊቶች ነው እያወራን ያለነው። በአሁኑ ጊዜም ልናደርጋቸው እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን ስላለፈው ጊዜ በተለየ ለማውራት 'used to' ን እንጠቀማለን።

2. እንዴት ነው የምመሰርተው?

አዎንታዊ ቅርፅ ይህ ነው
I used to play football. > ባለቤት + ዩዝድ ቱ + መሰረታዊ ግስ

አሉታዊ ቅርፁ ደግሞ ይሄ ነው
I didn’t use to play football. > ባለቤት + ዲድንት ዩዝ ቱ + መሰረታዊ ግስ

የጥያቄ ቅርፁ ይህ ነው
Did you use to play football? > ዲድ + ባለቤት + ዩዝ ቱ + መሰረታዊ ግስ

Careful! በአሉታዊ እና በጥያቄ ቅርፆች ላይ ከ ‘use’ ላይ ‘d’ ን እንዳልጨመርን ልብ ይበሉ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ‘did’ ሳላልን ነው። ይህ ግን አነባቡን አይቀይረውም።

3. ‘Used to’ የምንጠቀመው ከ ‘I’ ጋር ብቻ ነው?

No, አይደለም። የሁለተኛው ጥያቄ ላይ የቀረቡት ህግጋት ባለቤቱ የትኛውም ቢሆን ይሰራሉ።

I used to play football.
You used to play football.
He/ She used to play football.
We used to play football.
They used to play football.

4. ‘Used to’ የተለያዩ ትርጉሞች አሉት?

አዎ። ‘used to’ በገባበት አውድ መሰረት የተለያዩ ትርጉሞች ሊኖሩት ስለሚችል መጠንቀቅ አለብዎት። ስላለፈው ጊዜ ልማዶች፣ ስለዘወትር ተግባራት ስናወራ ተመሳሳዩን ቅርፅ እንደምንጠቀም ብቻ ያስታውሱ።

ስለልጅነት መዝናኛዎቼ ማውራት የምችለው እንዴት ነው?

4 Questions

Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ

Congratulations you completed the Quiz
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
x / y

Tell us what your childhood hobbies used to be on our Facebook group!
ስለልጅነት መዝናኛዎችዎ በፌስቡክ ቡድናችን ይንገሩን።

Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ ቋንቋ የምንማርበት እና የማዳመጥ ክህሎት የሚለማመዱበት How do I…, ዝግጅቶችን ለማዳመጥ በቀጣዩ ክፍል ይጠብቁን።

Session Vocabulary

 • play football
  እግር ኳስ መጫወት

  watch films 
  ፊልም ማየት

  listen to music
  ሙዚቃ ማዳመጥ

  a lot of
  ብዙ

  not… much 
  ብዙም አይደል