Unit 1: How do I...
Select a unit
- 1 How do I...
- 2 Unit 2
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 14
Listen to find out how to book an appointment.
ቀጠሮ እንዴት ማስያዝ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Activity 1
How do I book an appointment?
ቀጠሮ ስለማስያዝ የሚደረገውን ንግግር ያዳምጡና ቀጣዮቹን ጥያቄዎች ይመልሱ።
1. What day of the week is the appointment?
2. What time is the appointment?
መልስዎን ለማመሳከር ይሄንን ያዳምጡ። በመቀጠል ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያነፃፅሩት።

ዘሩባቤል
ሰላም፤ ይህ የ How do I… ዝግጅታችን ነው፤ አብረናችሁ የምንቆየው እኔ ዘሩባቤል እና ፊል ነን።
Phil
Hello, everybody. Welcome!
ዘሩባቤል
በዚህ ዝግጅት ቀጠሮ ማስያዝ እንዴት እንደሚቻል እንማራለን። አንድ ሰው ቀጠሮ ለማስያዝ ሲሞክር በማዳመጥ እንጀምር። ሁሉንም ነገር ባይረዱት ስጋት አይግባዎት፤ በኋላ ላይ እናግዝዎታለን። ለአሁኑ ግን ሴትዮዋ ቀጠሮ ማስያዝ ተሳክቶላት እንደሆነ ብቻ ይወስኑ።
Can I book an appointment for next Monday afternoon, please?
Yes, how about at 2:00pm?
Perfect. See you then.
ዘሩባቤል
ተናጋሪዋ ቀጠሮ ማስያዝ ተሳካላት? አዎ። ስለዚህ ፊል፥ ቀጥሮ ለማስያዝ የምንጠቀምበትን ቋንቋ እንመልከት?
Phil
Yes, good idea!
ዘሩባቤል
የመጀመሪያዋ ሴትዮ ቀጠሮ ለማስያዝ ፈልጋለች። ቀጠሮ የማያስያዣ ጥያቄዋን ምን በማለት ነው የጀመረችው? እናዳምጥ።
Can I book an appointment for next Monday afternoon, please?
Phil
Yes, we use the phrase ‘Can I…’ and combine it with ‘book an appointment?’ to make this request. Let’s practise it together. Repeat after me:
Can I book an appointment?
ዘሩባቤል
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ በጥያቄው ማብቂያ ላይ ቀጠሮውን መቼ ለማስያዝ እንደፈለገች ተናግራለች። ‘for next Monday afternoon’ ነው ያለችው ወይንስ ‘at next Monday afternoon’?
Can I book an appointment for next Monday afternoon, please?
Phil
It was ‘for’ next Monday afternoon.
ዘሩባቤል
አዎ፤ ቀጠሮ ማስያዝ የሚፈልጉበትን ጊዜ ለመግለፅ ‘for’ እና ቀጣይ ሳምንት ለማለት ደግሞ ‘next’ መጠቀም ይችላሉ። ከዚያ ቀኑን እና ሰዓቱን ‘morning’ ፥ ‘afternoon’ ፥ ‘evening’ የመሳሰሉ ቃላትን በመጠቀም መግለፅ እንችላለን። ስለዚህም ለሚቀጥለው ማክሰኞ ማለዳ ቀጠሮ ማስያዝ ቢፈልጉ. . .
Phil
You would say…
Can I book an appointment for next Tuesday evening, please?
Let’s practise the whole question together. Listen and repeat after me:
Can I book an appointment for next Monday afternoon, please?
Can I book an appointment for next Tuesday evening, please?
Can I book an appointment for next Wednesday morning, please?
ዘሩባቤል
አሁን ሁለተኛው ተናጋሪ ለቀጠሮው የትኛውን ሰዓት እንደጠቆመ እናዳምጥ።
Yes, how about at 2:00pm?
ዘሩባቤል
ከቀኑ ስምንት ሰዓትን ነው የጠቆመው፤ ሰዓቱን ለመጠቆምም ‘How about…?’ ብሏል። ይህንን ሐረግ ለመጠቆም እንጠቀምበታለን።
Phil
Let’s practise suggesting the time of the appointment. Listen and repeat after me:
How about at 2:00pm?
How about at 9:00am?
How about at midday?
ዘሩባቤል
በመጨረሻ የመጨረሻው ተናጋሪ በተባለው ሰዓት ተስማማች ወይንስ አልተስማማችም?
Perfect, see you then.
Phil
She agreed!
ዘሩባቤል
አዎ፤ ‘perfect’ በሚገባ እና ‘see you then’ ያኔ እንገናኛለን ነው ያለችው። የተባለውን ጊዜ ለመግለፅ ‘then’ እንጠቀማለን፤ በዚህ ምሳሌ ከቀኑ ስምንት ሰዓት መሆኑ ነው።
Phil
Let’s practise that final phrase. Repeat after me:
Perfect, see you then!
Great, now it’s time for some practice!
ዘሩባቤል
እሽ፤ ለረቡዕ ከሰዓት በኋላ ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ? በመጨረሻ ላይ ‘please’ ማለቶን አይዘንጉ። ከዚያ በኋላ መልስዎን ከፊል መልሶች ጋር ያመሳክሯቸው።
Phil
Can I book an appointment for Wednesday afternoon, please?
ዘሩባቤል
ጥሩ ሙከራ ነው፤ አሁን ደግሞ መልስ የሚሰጠውን ሰው ይሁኑና ለቀጠሮው ከቀኑ አስር ሰዓትን ይጠቀሙ። ከዚያም መልሶችዎን ከፊል መልሶች ጋር ያመሳክሩ።
Phil
Yes, how about at 4:00pm?
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ በዚያ ሰዓት ለመገናኘት እንስማማ። መጀመሪያ ላይ ‘perfect’ ማለቶን አይርሱ። ልክ እንደ ሁሌው መልስዎን ከፊል መልሶች ጋር ያነፃፅሩ።
Phil
Perfect. See you then!
Great, now you’re ready to make an appointment!
ዘሩባቤል
Well done, እና እባክዎን በቀጣዩ How do I… ዝግጅታችን ይጠብቁን።
Phil
Goodbye!
Learn more!
1. ቀጥሮ እንዴት ማስያዝ እችላለሁ?
ጥያቄ ለማቅረብ 'Can I' ማለት ይችላሉ ከዚያም 'book an appointment' የሚለውን ያስከትሉ።
- Can I book an appointment?
ቀጠሮው መቼ እንዲሆን እንደፈለጉ ለመግለፅ for የሚለውን ቃል በመጠቀም ከዚያም ቀጠሮ እንዲሆን የሚልጉበትን ዕለት እና ሰዓት ማስከተል ይችላሉ።
- Can I book an appointment for next Monday afternoon?
- Can I book an appointment for Tuesday evening?
2. ነገሮችን ለመጠቆም 'how about' መጠቀም የምችለው እንዴት ነው?
ይህንን ሐረግ መቼ መገናኛት እንዳለብን ለመጠቆም ልንጠቀምበት እንችላለን። ጊዜውን ለመገልፅ 'at'የተባለውን ቃል መጠቀምን ያስታውሱ።
- How about at 3:00pm?
- How about at 5:00pm?
የቀጠሮ ሰዓትን ከመጠቀም ባሻገር ing የሚያስከትል ግስን በመጠቀም ሌሎች ነገሮችን መጠቆም እንችላለን። በዚህ መሰረት የሚከተሉትን ነገሮች መጠቆም እንችላለን።
- How about meeting at 2:00pm?
- How about drinking coffee?
3. ጥቅም ላይ የሚውለው እንዴት ነው?
'Then'የሚያገለግለው በንግግር ውስጥ የተጠቀሰውን ጊዜ ለመግለፅ ነው። ስለዚህም የሆነ ሰው 'how about at 12:00pm? ቢል እና ስድስት ሰዓት ላይ ለመገናኘት ቢስማሙ 'see you then' ማለት ይችላሉ።
ቀጠሮ ማስያዝ የምችለው እንዴት ነው?
4 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
የትኛውን ረዳት ግስ ነው መጠቀም ያለብን? ዋናውስ ግስ ይቀየራል?Question 1 of 4
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
የሚያስፈልግዎት መስተዋድድ ከአንድ ነገር ጋር በተያያዘ ያለን ነገር ለመግለፅ የሚጠቅም ነው።Question 2 of 4
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
አንድ ነገር ሌላኛውን ተከትሎ የሚመጣ መሆኑን የሚጠቁም ቃል ነው።Question 3 of 4
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
'Appointment' የሚለውን ቃል የመጀመሪያ ድምፅ እና አንድ ነገር መታቀዱን ለመግለፅ የምንጠቀምበትን መስተዋድድ ያስቡ።Question 4 of 4
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
How about joining our Facebook group and learning English everyday!
የፌስቡክ ቡድናችንን ቢቀላቀሉና እንግሊዝኛ ቢማሩ ምን ይመስልዎታል?
Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ ቋንቋ የምንማርበት እና የማዳመጥ ክህሎትዎን የሚለማመዱበትን How do I…ዝግጅቶችን ለማዳመጥ በቀጣዩ ክፍል ይጠብቁን።
Session Vocabulary
book
ቀድሞ ማስያዝappointment
ቀጠሮHow about…?
ምን ይምስልዎታልPerfect!
በሚገባ/ትክክልSee you then.
ያኔ እንገናኝ