Learning English

Inspiring language learning since 1943

English Change language

Session 13

Listen to find out how to talk about how you feel.
ስለሚሰማዎት ስሜት እንዴት ማውራት እንደሚችሉ ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።

Sessions in this unit

Session 13 score

0 / 4

 • 0 / 4
  Activity 1

Activity 1

How do I talk about how I feel?

ምንም እንኳን ‘-ed’ በበርካታ ቃላት መጨረሻ ላይ የሚገባ ቢሆንም፥ የሚነበብባቸው ልዩ ልዩ መንግዶች አሉ።

የሚቀጥሉት ቃላት የመጨረሻ ድምፆች ምንድን ናቸው?

relaxed
bored
excited

መልስዎን ለማመሳከር ይሄንን ያዳምጡ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያወዳድሩ።

Show transcript Hide transcript

ዘሩባቤል
ሰላም፥ ይህ የ How do I ዝግጅታችን ነው፤ አቅራቢያችሁ እኔ ዘሩባቤል አብሮኝ ደግሞ ቶም አለ።

Tom
Hello, everybody. Welcome to today’s episode!

ዘሩባቤል
በዚህ ዝግጅት ስለሚሰማን ስሜት የምናወራባቸውን ልዩ ልዩ መንገዶች እንመለከታለን። ሁሉም ነገር ግልፅ ባይሆንልዎት ብዙም ስጋት አይግባዎት፤ በኋላ ላይ እናግዝዎታለን። ለአሁኑ ሦስቱን ተናጋሪዎች ያዳምጡ። ምን ዓይነት ስሜትን ነው የሚገልፁት?

I’m relaxed because I have the day off.
I’m bored because I don’t have anything to do.
I’m excited because it’s the weekend.

ዘሩባቤል
ልብ አሉት? የመጀመሪያው ተናጋሪ ‘relaxed’ ዘና ማለትን ነው የገለፀው፤ ሁለተኛዋ ‘bored’ መሰላቸት፤ ሶስተኛዋ ደግሞ ‘excited’ መደሰትን ነው የገለጸችው።

Tom
But they also provide reasons about why they feel this way.

ዘሩባቤል
So, Tom ስሜቶቻችን እንዴት መግለፅ እንደምንችል ለመመልከት ዝግጁ ነህ?

Tom
Yes, I am. Let’s do that!

ዘሩባቤል
በመጀመሪያ ተናጋሪዎቹ ‘I’m’ ብለው ነው ንግግራችውን የጀመሩት ከዚያም ስሜትን የሚገልፅ ቃል አስከትለዋል። አነባበቡን ታሳያቸዋለህ ቶም?

Tom
Of course! All the words used by the speakers to describe feelings end in the letters ‘-ed’, but these have different sounds!
Listen to the first speaker.

I’m relaxed because I have the day off.

‘Relaxed’ ends in a /t/ sound. Say it with me:
relaxed

ዘሩባቤል
አሁን ሁለተኛውን ተናጋሪ ያዳምጡ፤ የሁለተኛው ቃል የመጨረሻ ድምጽ ምንድን ነው?

I’m bored.

Tom
Did you get it? Bored ends with a /d/ sound. Say it with me:
bored

ዘሩባቤል
አሁን የመጨረሻውን ተናጋሪ ያዳምጡ፤ የስሜት ገላጩ ቃል የመጨረሻ ድምፅ ምንድን ነው?

I’m excited.

Tom
That one was a strong sound! Excited ends with an /Id/ sound. Say it with me:
excited

ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! ግሩም አንባበብ! ሁሉም ተናጋሪዎች ያሏቸውን ስሜቶች ገልፀዋል። እነዚህ ስሜቶች በሁኔታዎች ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ያንን ሁኔታ ለማስተዋወቅ ‘because’ የሚለውን ቃል ተጠቅመዋል። እስኪ እናዳምጥ።

I’m relaxed because I have the day off.

ዘሩባቤል
የመጀመሪያው ተናጋሪ ‘the day off’ የአንድ ቀን እረፍት ላይ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ‘relaxed’ ዘና ብሏል። በዚህኛው አጋጣሚ የአንድ ቀን እረፍት እንደመውሰድ ያለ አንዳች ዓይነት ስሜትን የሚፈጥርብዎትን ሁኔታ መግለፅ ሲፈልጉ ‘-ing!’ መጨመር ይችላሉ።

Tom
That’s right! A day off makes us feel ‘relaxed’. So, a day off is ‘relaxing’.
Say it again with me:
relaxing

ዘሩባቤል
Excellent! አሁን የመልመጃ ጥያቄ ሰዓት ነው! ተናጋሪዎቹ ስሜቶቻቸውን ለመግለፅ ምን ዓይነት ቅፅሎችን ተጠቅመዋል?

I’m bored because it’s Monday.

አንዳች ዓይነት ስሜት ስለሚፈጥሩብን ነገሮች ስናወራ ‘-ing!’ ከጨመርን ሰኞዎችን እንዴት እንገልፃለን?
አረፈተ ነገሮቹን ከእኔ ጋር ይሙሏቸው።

Mondays are ________.

Tom
‘Boring’. Did you get it? Say it again with me:
Mondays are boring.

ዘሩባቤል
Good job! ስለዚህ አሁን ሦስተኛውን ተናጋሪ በመጠቀም ሌላ ጥያቄ እንሞክር። ይህኛው ተናጋሪ ምን ዓይነት ስሜት አላቸው?
I’m excited because it’s the weekend.

Tom
So, the weekend makes him feel ‘excited’. How can we describe the weekend using ‘–ing’?

That’s right! Exciting! Say it with me:
The weekend is exciting.

ዘሩባቤል
Nice work! ያስታውሱ፤ የሆነ ነገር አንዳች ዓይነት ስሜት ሲፈጥርብዎት ‘-ing!’ ይጠቀማሉ። ለምሳሌ እንግሊዝኛን መማር ‘exciting’! ነው ማለት እችላለሁ።

Tom
That’s right! Learning is ‘exciting’, which means that I’m ‘excited’!

ዘሩባቤል
ከመሰናበታችን በፊት የቃላቱን አነባበብ ለመጨረሻ ጊዜ ከቶም እናዳምጥ።

Tom
Relaxed, bored and excited.
and
Relaxing, boring, exciting.

ዘሩባቤል
በቀጣዩ ‘exciting’ መሰናዷችን ለመገናኘት ‘excited’ እንደሆናችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። See you then!

Tom
See you then everybody! Bye!

Learn more!

1. ስሜቶቻችንን ለማስተዋወቅ የትኞቹን ቃላት እንጠቀም
ስሜታችንን ከመግለፃችን በፊት ‘I feel’ መጠቀም እንችላለን።

2. ሁሉምን ስሜትን የሚገልፁ ቃላት ሁሉ በ–ed ነው የሚጨርሱት?
አይደለም’፤ ምንም እንኳ የተለመደ አጨረረስ ቢሆንም።
እነዚህን ሁለት አጨራረሶች ከገላጭ ቃላት ወይንም 'adjectives' ከቅፅሎች ጋር እንጠቀማቸዋለን።

በ-ed የሚያልቁ ያሉንን ስሜቶች ይገልፃሉ
በ-ing የሚያልቁ አጨራረሶች አንዳች ስሜት የፈጠሩብንን (መንስዔዎች) ይገልፃሉ።

I am excited about learning a new language.
Learning a new language is exciting.

ስለሚሰማኝ ስሜት እንዴት መናገር እችላለሁ?

4 Questions

Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።

Congratulations you completed the Quiz
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
x / y

Tell us how you’re feeling (and why) on our Facebook group!
ምን ዓይነት ስሜት እንዳለዎት (እና ለምን እንደዚያ እንደሆነ) በፌስቡክ ቡድናችን ይግለፁልን።

Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ ቋንቋ የምንማርበት እና የማዳመጥ ክህሎትዎን የሚለማመዱበትን How do I…ዝግጅቶችን ለማዳመጥ በቀጣዩ ክፍል ይጠብቁን።

Session Vocabulary

 • relaxed
  ዘና ያለ

  relaxing
  ዘና የሚያደርግ

  bored
  የተሰላቸ

  boring
  አሰልቺ

  excited
  የተደሰተ

  exciting
  አስደሳች

  weekend
  የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት

  day off
  የእረፍት ቀን

  (to have) nothing to do
  ምንም የሚያደርጉት ነገር ያለመኖር