Learning English

Inspiring language learning since 1943

English Change language

Session 11

Listen to find out how order food and drink in a restaurant.
ምግብ ቤት ውስጥ ምግብ እንዴት ማዘዝ እንደሚችሉ ለመረዳት ማዳመጥዎን ይቀጥሉ

Sessions in this unit

Session 11 score

0 / 4

 • 0 / 4
  Activity 1

Activity 1

How do I order food and drink in a restaurant?

ምግብ ቤት ውስጥ ምግብ ለማዘዝ የምንጠቀምበትን ሐረግ ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ ሁለቱን ቃላት ያዛምዱ።

For      drink
For main
To dessert
To start

መልሶችዎን ለማጣራት ማዳመጥዎን ይቀጥሉ። በመቀጠል ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያወዳድሩት።

Show transcript Hide transcript

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ወደ How do I… ዝግጅታችን በደህና መጡ። አዘጋጆች እኔ ዘሩባቤል አብራኝ ደግሞ. . .

Sam
And me, Sam. Hello, everybody.

ዘሩባቤል
በዚህ ክፍል ምግብ ቤት ውስጥ ምግብ እንዴት ማዘዝ እንደሚቻል እናያለን። በቅድሚያ እስኪ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ያለ ሰው እናዳምጥ። ሁሉም ነገር ባይገባዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ በኋላ እናግዝዎታለን። ለአሁኑ ተጠቃሚው ምን ኤእነት ምግቦች እንዳዘዘ ብቻ ይወስኑ፤ ለእሱ የሚያግዝዎት ቃላት ደግሞ እነሆ፤ ‘soup’ ሾርባ፥ ‘fish’ ዓሣ፥ ‘vegetables’ አትክልት፥ ‘chocolate cake’ የቼኮሌት ኬክ እና ‘water’ ውሃ።

Waiter: Are you ready to order?
Diner: Yes! To start, I’ll have the soup, please. For main, I’ll have the fish with vegetables. And for dessert, I’ll have the chocolate cake, please.
Waiter: Of course. Anything to drink?
Diner: To drink, I’ll have water, please.

ዘሩባቤል

አዳመጡ? ተጠቃሚው ሶስት አይነት ምግብ ነው ያዘዙት። So, Sam, shall we look at the language we can use to order in a restaurant?

Sam
Absolutely!

ዘሩባቤል
ስለዚህም አስተናጋጁ የጠየቀው የመጀመሪያው ጥያቄ ‘Are you ready to order?’ የሚል ነበር።

Sam
There are only two ways to answer this question: ‘yes’ or ‘no’! In our conversation, the answer was ‘yes’.

ዘሩባቤል
አንድ ሰው እንዴት እንደሚያዝዝ ደግመን እናዳምጥ እና ሦስቱን ዙሮች እንዴት እንደሚያጠቅሷቸው እንለይ፤ አንደኛቸው ከሌሎቹ ከሁለቱ የተለዩ ናቸው።

Yes! To start, I’ll have the soup, please. For main, I’ll have the fish with vegetables. And for dessert, I’ll have the chocolate cake, please.

ዘሩባቤል

ልዩ የነበረው ምን እንደሆነ ልብ አሉ? እያንዳንዱን ዙር የምናስተዋውቀው እንዲህ ነው፡ ‘to start’ ለመጀመር ፥ ‘for main’ ዋናውን ምግብ እና ‘for dessert’ ጣፋጭ ነገር።
‘To start’ ድርጊት ሲሆን ‘main’ እና ‘dessert’ ግን ስሞች ናቸው፤ ስለዚህም ‘for’ እጠቀማለን እንጂ ‘to’ አንጠቀምም።

Sam
And then you say what you want – do you remember how?

ዘሩባቤል
አዎ፤ ‘I’ll have…’ የምፈልገው፤ እዚህ ላይ አሁን ስለምናከናውነው እርምጃ ለማውራት ከ 'have' ጋር ‘I’ll’ እንጠቀማለን።

Sam
Yes, decisions in a restaurant are usually quite quick. And after ‘I’ll have…’ you say the food or drink you want.

ዘሩባቤል
እናም ደግሞ ከምናዘው ምግብ በፊት ‘the’ እንደምንጠቀም ልብ ይበሉ፤ ለዚህም ምክንያቱ በምግብ መዘርዝሩ ውስጥ ስላለው አንድ ውስን ዓይነት እያወራን ስለሆነ ነው። ለመለማመድ ሳምን ያዳምጡ።

Sam
Repeat after me:
To start, I’ll have the soup, please.
For main, I’ll have the fish with vegetables.
And for dessert, I’ll have the chocolate cake, please.

ዘሩባቤል
ቀጥሎ የሚጠጣ ምን ይወስዱ እንደሆነ ‘Anything to drink?’ በማለት ይጠይቅዎታል፤

Sam
Yes – this is short for ‘would you like anything to drink? – and how do you answer it, do you remember? Let’s listen again:

To drink, I’ll have water, please.

ዘሩባቤል
ስለዚህም ‘to drink’ ልክ ‘to start’ በተጠቀምንበት መልኩ እንጠቀማለን፤ ምክንያቱም የሚገልፀው ድርጊት ነው፤ ተከሎትም ‘I’ll’ ይመጣል።

Sam
Great! Now you’ve learned what to say in a restaurant, it’s time for you to practise.

ዘሩባቤል
በመጀመሪያ አስተናጋጁ ለማዘዝ ዝግጁ መሆን ያለመሆንዎትን ይጠይቅዎታል። ለመጀመሪያው ዙር የሚፈልጉት ሾርባውን ነው። ያስታውሱ ‘for’ አንጠቀመም። እናም ትሁት ለመሆን ይሞክሩ። ከዚያ መልስዎትን ከሳም ጋር ያነፃፅሩ።

Sam
To start, I’ll have the soup, please.

ዘሩባቤል
ቀጥሎ የሚፈጉት ዓሣ ነው። ምን ይላሉ?

Sam
For main, I’ll have the fish.

ዘሩባቤል
ተመሳሳይ ነገር ነው ያሉት?
በመጨረሻም ለአስተናጋጁ ጥያቄ ውሃ ብለው ይመልሱና መልስዎትን ከሳም ጋር ያነፃፅሩ።

Anything to drink?

Sam
To drink, I’ll have water, please.

ዘሩባቤል
Ok, so now you know how to order food and drink in a restaurant. ታዲያ ይሄንን ለምን ከጓደኛዎ ጋር አይለማመዱትም?

Sam
Yes, and see you next week. Bye!

ዘሩባቤል
Bye!

Learn more! 

1. ለምንድን ነው 'to start' ብለን 'for main' የምንለው?
'Start' እና 'drink' ድርጊትን የሚገልፁ ግሶች ናቸው። ስለዚህም ከፊታቸው to እንጠቀማለን። ‘Main’ እና ‘dessert’ ደግሞ ነገሮች ወይንም ስሞች ስለሆኑ ከፊታቸው የምንጠቀመው 'for' ነው።

2. እነዚህ ሐረጎች በአረፍተ ነገር ውስጥ የሚገቡት የት ነው?
በአረፈተ ነገሩ መጀመሪያ ላይ ሊመጡ ይችላሉ። ለምሳሌ 'For main, I’ll have the fish, please' እንላለን። ወይንም ደግሞ ከምግብ በኋላ ሊመጡ ይችላሉ። ለምሳሌ 'I’ll have the fish for main, please.'

3. በትህትና ‘እፈልጋለሁ’ ለማለት ስንፈልግ የምጠቀምበት ሐረግ ምንድን ነው?
ምግብ ቤቶች ውስጥ በምናዝበት ወቅት 'I’ll have…, please' እንላለን።
የሚከተሉትንም መጠቀም ይችላሉ፡
Can I have…, please?
I’d like…, please.

4. ምግብ ቤት ውስጥ ስናዝዝ ከምግብ በፊት 'the' የምንጠቀመው ለምንድን ነው?
ከምግብ ዝርዝሩ ላይ ምግብ ስናዝዝ 'the' አብረን እንጠቀማለን፤ ለዚህም ምክንያቱ የተወሰነ ነገር ስለሆነ እና ስለየትኛው 'fish' ወይንም 'soup' እንደምናወራ ሁሉም ሰው ስለሚያውቅ ነው። ስለእነዚህ ምግቦች በጥቅሉ እያወራን ከሆነ ግን ከፊታቸው 'the' አንጠቀምም።

ምግብ ቤት ውስጥ እንዴት ማዘዝ እችላለሁ?

4 Questions

Arrange the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።.

Congratulations you completed the Quiz
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
x / y

What's your favourite type of restaurant? Why? Tell us on our Facebook group!
የሚመርጡት ምግብ ቤት ምን ዓይነት ነው? ለምን? በፌስቡክ ቡድናችን ይንገሩን።

Join us for our next episode of How do I… when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ጠቃሚ ቋንቋዎችን ለመማርና የማዳመጥ ክህሎትዎን በልምምድ ለማዳበር ቀጣዩን How do I… ዝግጅታችንን ይከታተሉ።

Session Vocabulary

 • the soup
  ሾርባውን

  the fish
  ዓሣ

  with vegetables
  ከአትክልት ጋር

  the chocolate cake
  የቼኮሌት ኬክ

  water
  ውሃ