Learning English

Inspiring language learning since 1943

English Change language

Session 1

Listen to find out how to start a conversation when meeting new people in English.
አዳዲስ ሰዎችን ሲገናኙ በእንግሊዝኛ እንዴት መነጋገርን መጀመር እንደሚችሉ ለማወቅ ያዳምጡ።


Sessions in this unit

Session 1 score

0 / 4

 • 0 / 4
  Activity 1

Activity 1

How do I start a conversation?

አዳዲስ ሰዎችን ስናገኝ የምንጠይቃቸውን የተለመዱ ሶስት ጥያቄዎች ከምላሾቻቸው ጋር ያዛምዱ።

a) What’s your name? 1. I’m from Liverpool.
b) Where are you from? 2. I’m a teacher.
c) What do you do? 3. Hello, I’m Lisa.

     

መልሶችዎን ለማጣራት ማዳመጥዎን ይቀጥሉ። ከዚያ ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያወዳድሩት።

Show transcript Hide transcript

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ወደ ‘How do I…’ዝግጅታችን መጡ። አዘጋጆች እኔ ዘሩባቤል እና ሳም ነን።

Sam
Hello, everybody. Welcome!

ዘሩባቤል
በዚህ ክፍል ከማናውቃቸው ሰዎች ጋር እንዴት ውእይት እንደምንጀምር እንመለከታለን። ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገናኙ ሰዎች አጭር ውይይት ሲያደርጉ በማዳመጥ እንጀምር። ሁሉም ካልገባዎት ብዙም አይጨነቁ፤ በኋላ እናግዝዎታለን። ለአሁኑ ግን ሮበርት ከሊሳ የፈለጋቸውን ሦስት መረጃዎች ያስተውሉ።

Robert
Hi, my name’s Robert. What’s your name?
Lisa
Hello, I’m Lisa. Nice to meet you.
Robert
Nice to meet you, too, Lisa. Where are you from?
Lisa
I’m from Liverpool.
Robert
And what do you do?
Lisa
I’m a teacher.

ዘሩባቤል
የተባለውን ሰሙ? አዎ፥ ሮበርት ሊሳን የጠየቃት ስሟን፥ ከየት እንደመጣች እና ስራዋ ምን እንደሆነ ነው። ስለዚህ ሳም አዳስ ከምንተዋወቃቸው ሰዎች ጋር የምንጠቀመውን ቋንቋ እንመልከት?

Sam
Yes, let’s!

ዘሩባቤል
ስለዚህ፥ ሮበርት እና ሊሳ መጀመሪያው ያደረጉት ራሳቸውን ማስተዋወቅ ነው። ተመሳሳይ መንገድን ነው የተጠቀሙት? እስቲ እንደገና እናዳምጥ።

Hi, my name’s Robert.
Hi, my name’s Robert.
Hello, I’m Lisa.
Hello, I’m Lisa.

ዘሩባቤል
አይደለም፤ የተለያዩ መንገዶችን ነው የተጠቀሙት! ‘My name is…’ እና ‘I’m…’.

Sam
And the pronunciation is important here, so let’s quickly practise - repeat after me:
‘My name’s…’
‘I’m…’

ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! አሁን ሮበርት ከሊሳ ጋር የነበረውን ውይይት ወዳስቀጠለበት መንገድ እንሂድ። ሦስት ጥያቄዎችን ነው የጠየቃት። እስቲ እንደገና እንስማቸው።

What’s your name?
What’s your name?
Where are you from?
Where are you from?
What do you do?
What do you do?

ዘሩባቤል
እሽ። የመጀመሪያው ጥያቄ የሊሳን ስም መጠየቅ ነው፤ ሁለተኛው ከየት እንደመጣች፥ ሦስተኛው ደግሞ ስለ ስራዋ ነው።

Sam
Yes, these are the most common questions to ask someone when you first meet them, so they’re very useful. But the pronunciation is important. You need to sound interested!

ዘሩባቤል
አዎ፥ የአነጋገር ቅላፄ ወሳኝነት አለው! እንዲሁም የትኞቹ ቃላት ላይ አፅንዖት ሰጥተው እንደሚናገሩ እንዲሁም ቃላቱ የሚጠብቁበት መንገድ አስፈላጊ ነው።

Sam
Yes, so let’s quickly practise together! Repeat after me:
‘What’s your name?’
‘Where are you from?’
‘What do you do?’

ዘሩባቤል
ሊሳ ለእነዚህ ጥያቄዎች እንዴት ምላሽ ሰጠች? ‘What’s your name?’ የሚለውን ጥያቄ መመለሻ ሁለት መንገዶች እንዳሉ አይተናል። ‘Where are you from?’ እና ‘What do you do?’ የሚሉትን ጥያቄዎች እንዴት ሊዛ እንዴት እንደመለሰች ለመለየት ደግመን እናዳምጥ።

I’m from Liverpool.
I’m from Liverpool.
I’m a teacher.
I’m a teacher.

Sam
So, Lisa used ‘I’m’ to answer both questions.

ዘሩባቤል
አዎ፥ ነገር ግን ‘I’m from…’ ካሉ እያወሩ ያሉት ስለቦታ ነው ማለት ነው።

Sam
And if you say ‘I’m a…’ you’re talking about your job. Remember to use the ‘a’, as it’s important here.

ዘሩባቤል
Thanks, Sam! አሁን ልምምድ የሚያደርጉበት ጊዜ ነው። እኝህ ሰው ቀደም ሲል ለቀረቡት ሶስት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ያዳምጡ።

I’m from Cambridge.
I’m from Cambridge.

ዘሩባቤል
'Cambridge' የቦታ ስም ነው። ስለዚህ እኝህ ሰው የትኛውን ጥያቄ ነበር የተጠየቁት ማለት ነው? ከቆይታ በኋላ ሳም መልስ ስትሰጥ ይሰማሉ።

Sam
Where are you from?

ዘሩባቤል
Good! አሁን የዚህን ሰው ምላሽ ያዳምጡ

I’m a taxi driver.
I’m a taxi driver.

ዘሩባቤል
‘A taxi driver’ የስራ ዓይነት ነው፤ ስለዚህ ትክክለኛው ጥያቄ ምንድን ነው?

Sam
What do you do?

ዘሩባቤል
Great! ስለዚህ አሁን ከአዳዲስ ሰዎች ጋር ንግግር እንዴት መጀመር እንደሚችሉ አውቀዋል። ሁላችሁንም ስላወኳቹ ደስ ብሎኛል። Nice to meet you all!

Sam
Yes, nice to meet you!

ዘሩባቤል
በሚቀጥለው ሳምንት ሌላ 'How do I…' ዝግጅት ይዘን እንመጣለን፤ ይጠብቁን።

Sam
Bye! 

Learn more!

1. 'My name’s...' እና 'I’m…' ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው?
አዎ።

2. 'Nice to meet you' ን መቼ ነው የምጠቀመው? 'Nice to meet you, too' ንስ?
'Nice to meet you, too' ን አንድ ሰው 'Nice to meet you' ካለን በኋላ በምላሽነት እንጠቀመዋለን። 'too' ም፥ እንደዚያው፥ በተመሳሳዩ 'also' ማለት ነው።

3. 'Where are you from?' የሚለውን ጥያቄ ስመልስ 'from' ን ማስቀረት እችላለሁ?
አንችልም፤ ይሄንን ጥያቄ ስንመልስ ሁሌጊዜም fromን እንጠቀማለን። ከመንደሮች፥ ከአገራት፥ ከክልሎች እና ከአጠቃልይ ቦታዎች ፊት ሊጠቀሙት ይችላሉ።
I’m from London.
I’m from the UK.
I’m from the coast (ዳርቻው).

4. ከስራዎች በፊት 'a' ን መጠቀም አለብኝ?
አዎ፥ ሁሌም ከነጠላ የሚቆጠር ስም በፊት aን መጠቀም አለብን።

How do I start a conversation?

4 Questions

Choose the correct answer.

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።

Congratulations you completed the Quiz
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
x / y

Nice to meet you!
What’s your name?
Where are you from?
What do you do?

Answer these questions and tell us on our Facebook group!
ጥያቄዎችን ይመልሱና በፌስቡክ ቡድናችን ላይ ይንገሩን።

Join us for our next episode of 'How do I…', when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ አጠቃቀሞችን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ 'How do I...' ክፍላችን ይጠብቁን።

Session Vocabulary

 • What’s your name?
  ስምህ/ሽ ማን ነው?

  My name’s…
  ስሜ...ይባላል።

  I’m…
  ...ነኝ።

  Nice to meet you.
  ስላገኘሁህ/ሽ ደስ ብሎኛል።

  Nice to meet you, too.
  እኔም ስላገኘሁህ/ሽ ደስ ብሎኛል።

  Where are you from?
  የት ነው የምትኖረ/ሪው? ከየት ነው የመጣኸ/ሽው?

  I’m from…
  ...ነው የመጣሁት።

  What do you do?
  ምን ትሰራለህ/ትሰሪያለሽ?

  I’m a...
  ...ነኝ።