Learning English

Inspiring language learning since 1943

English Change language

Session 9

Listen to find out how to respond to news.
ሰው ለሚነግረን ዜና እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚቻል ለማየት ይሄንን ያዳምጡ።

Sessions in this unit

Session 9 score

0 / 3

 • 0 / 3
  Activity 1

Activity 1

How do I respond to news?

Listen to find out how to respond to news.
ለዜና እንዴት መመለስ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።

መልስዎን ለማመሳከር ይሄንን ያዳምጡ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያመሳክሩት።

Show transcript Hide transcript

ምህረተስላሴ
ወደ ‘How do I…’ ዝግጅታችን እንኳን በደህና መጡ። የምናቀርብላችሁ እኔ ምህረተስላሴና ሳም ነን።

Sam
Welcome, everybody! Hello.

ምህረተስላሴ
በዚህ ዝግጅታችን ሰዎች አንዳች ዜና ሲነግሩን ምላሽ ስለምንሰጥባቸው መንገዶች እንማራለን። ዴቪድ እና ሜጋን የሚለዋወጡትን ሶስት ንግግር በማዳመጥ እንጀምር። የሚያወሩት ግልፅ አልሆን ካለዎት አይስጉ፤ ኋላ እናግዝዎታለን። ለአሁኑ የዴቪድን ዜና ያዳምጡና ምን ዓይነት ፈተና 'test' እንደወሰደ ይወስኑ።

David
I’m nervous. I'm taking my driving test this afternoon!

Megan
Good luck! Hope it goes well.

David
The driving test was terrible. I failed!

Megan
Oh, I'm sorry to hear that. Better luck next time!

David
The driving test was fine this time. I passed!

Megan
Well done. Congratulations!

ምህረተስላሴ
ዴቪድ የወሰደው የመንጃ ፈቃድ ፈተና ነው። ዴቪድ የተለያየ ዓይነት ዜና ሲኖረው ሜጋን ለእያንዳንዱ ዜና በልዩ ሁኔታ ምላሽ መስጠት አለባት።

በመጀመሪያው ንግግር ዴቪድ የመንጃ ፈቃድ ፈተና ለወደፊት እንደሚወስደው ለሜጋን ነግሯታል። ደግመው ያዳምጡ፤ ሜጋን የተጠቀመቻቸው ሁለት ሐረጎች ምንድን ናቸው?

Good luck! Hope it goes well.

ምህረተስላሴ
ሜጋን 'Good luck!' ብላዋለች። መልካም ዕድል ማለት ነው። 'Hope it goes well' ብላለች። ውጤቱ ጥሩ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ ማለት ነው።'Hope it goes well' ውስጥ ያለው ‘it’ የዴቪድን ፈተና ያመላክታል። ዴቪድ ከአንድ በላይ ፈተና ነበረው እንዴ?

Sam
You would say 'they' – 'Hope they go well!'

ምህረተስላሴ
እነዚህን ሁለት ሀረጋት ሁሌም አንድ ላይ አንላቸውም። አይደል እንዴ ሳም?

Sam
Oh no, you can just say one!

Now, let's practise the pronunciation! Repeat after me:

Good luck!

Hope it goes well!

Let's listen to Megan again. This time it's bad news!

Oh, I'm sorry to hear that. Better luck next time.

ምህረተስላሴ
አሁንም ሁለት ሐረጎች አሉን። ለየብቻቸው ወይንም አንድ ላይ ልንጠቀማቸው እንችላለን። ሜጋን ዴቪድ ለነገራት መጥፎ ዜና በሀዘኔታ ምላሽ ሰጥታለች።

Sam
…and if you want to make this stronger, say: 'I'm so sorry to hear that!'

ምህረተስላሴ
በሁለተኛው ንግግር 'Better luck next time' ብላለች። በቀጣይ በጎ ነገር ይግጠምህ ማለት ነው። ይህንን አባባል ሲጠቀሙ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። አንድ ሰው ሙከራ አድርጎ ሳይሳካለት ሲቀር ብቻ ነው ሊጠቀሙት የሚገባው። ለምሳሌ አንድ ሰው ውሻው ቢሞትበት አባባሉን መጠቀም አይችሉም።

Sam
Quick practice of pronunciation – repeat after me:

I'm sorry to hear that.

Better luck next time.

ምህረተስላሴ
አሁን ደግሞ ለመልካም ዜና ምላሽ የሚሰጥባቸውን ሐረጎች ደግመው ያዳምጡ። Here's Megan.

Well done. Congratulations!

ምህረተስላሴ
'Well done' የሚለውን እንደሚያውቁት እንገምታለን፤ ምክንያቱም በእያንዳንዱ ዝግጅታችን ጥሩ ስራ ሲያከናውኑ በጣም ጥሩ/ጎበዝ እያልን እናበረታታዎታለን።

Sam
Yes! You can also say 'Good work!', 'Good job!', 'Excellent!', 'Amazing!', 'Wonderful!'

ምህረተስላሴ
'Congratulations ከ 'Well done' በበለጠ የሚያስፈልግበት ጊዜ አለ። ለሰርግ፣ ልጅ ሲወለድ እና የስራ ዕድገት ሲገኝ ያገለግላል።

Sam
Absolutely! Time to practise the pronunciation. Repeat after me: 

Well done!

Congratulations!

ምህረተስላሴ
ሰዎች ለሚነግሯችሁ ዜናዎች እንዴት ምላሽ እንደምትሰጡ ተምራችኋል። አሁን መለማመጃ ሰዓት ላይ ደርስናል።

ጓደኛዎ ስለ እጣ 'lottery'  የተመለከተ ዜና ሲነግርዎ ያዳምጡ። ምላሽ የሚሰጡት እንዴት ነው? ኋላ ላይ የሳምን ምላሽ ያዳምጣሉ።

I just won the lottery! I'm so happy!

Sam
Congratulations!

ምህረተስላሴ
Excellent! ጓደኛዎ ስላጣው 'lost' ሲነግርዎት ያዳምጡ። እዚህ ላይ ከሌላው ይልቅ የሚያስፈልግ አንድ ሐረግ እንዳለ ልብ ይበሉ።

I lost my dog! I'm so sad.

Sam
I'm so sorry to hear that!

ምህረተስላሴ
ተመሳሳይ ነገር ነው ያሉት?

Sam
Yes, and congratulations, and good luck! Bye bye, everyone!

ምህረተስላሴ
በሚቀጥለው የ ‘How do I…’  ዝግጅት ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!

Learn more!

1) ለሰዎችወደፊትመልካምዕድልእንዲገጥማቸውየምመኘውእንዴትነው?

ለሰዎች መልካም ምኞትን ለማስተላለፍ የሚያገለግሉ የተለመዱ ሐረጋት እነዚህ ናቸው

 • Good luck! መልካምዕድል
 • Hope it goes well!

ጥሩእንደሚሆንተስፋአለኝ

 ‘I hope…’ ወይምHopeብቻንመጠቀምይችላሉ።it’ የተባለውተውላጠስምደግሞአንድንነገርለምሳሌፈተናንያመላክታል።

 • Hope they go well!ጥሩእንደሚሆኑተስፋአለኝ።

‘I hope…’ ወይምHopeብቻንመጠቀምይችላሉ።they’ የተባለውተውላጠስምደግሞከአንድበላይነገርንነገርለምሳሌበርካታፈተናዎችንያመላክታል። 

 • All the best! መልካሙሁሉይግጠምህ/
 • Best of luck! መልካምዕድል

2) ለመጥፎዜናምላሽየሚሰጠውእንዴትነው?

ሰዎች መጥፎ ዜና ሲነግን ሀዘኔታችንን የምንገልፅባቸው የተለመዱ ሐረጋት እነዚህ ናቸው

 • I’m sorry to hear that.እርሱንስለሰማሁአዝኛለሁ

sorryበፊት‘so ወይንም‘so very’ በማስገባትስሜትዎንጠንከርማድረግይችላሉ።ይህሐረግበማንኛውምአውድያገለግላል።

 • Better luck next time. በሚቀጥለውየተሻለዕድልይግጠምህ/

Variations of this are ‘I wish you better luck next time!’ or ‘I hope you have better luck next time!’ የዚህአገላለፅሌሎችርቢዎች  ‘I wish you better luck next time!’ ወይንም‘I hope you have better luck next time!’ናቸው።

ይህንንሐረግለመጠቀምየበለጠተገቢየሚሆነውአንድሰውእንድንሙከራአድርጎሳይሳካለትሲቀርነው።ይህንንሐረግለሞትወይንምለእጦትዜናምላሽአድርገንልንጠቀመውአንችልም።

3) ሰዎችመልካምዜናዎችንሲናገሩምላሽየምንሰጠውእንዴትነው?

ሰዎች መልካም ዜና ይዘው ሲመጡ ደስታችንን ለማሳየት የምንጠቀምባቸው የተለመዱ ሐረጋት እነዚህ ናቸው

 • Congratulations!እንኳንደስአለሽ/

ይህሐረግበየትኛውምአውድውስጥሊያገለግልይችላል።ለሰዎችመልካምኩነቶችምለምሳሌለሰርግልጅለመውለድእናለስራዕድገትያገለግላል።የሚከተሉትምበበርካታአውዶችላይይጠቅማሉ።

 • Excellent!
 • Amazing!
 • Wonderful!
 • Well done! ጎበዝ
 • Good work! ድንቅስራ
 • Good job ግሩምስራ!

እነዚህንሐረጎችመጠቀምተገቢየሚሆነውአንድሰውአንዳችዓይነትስኬትሲያስመዘግብነው።ለምሳሌለሚያገባሰውየሰርጉዕለት Well done! ቢሉትነገሩእንግዳይሆናል።

ሰው ለሚነገረን ዜና ምላሽ የምሰጠው እንዴት ነው?

3 Questions

Choose the correct option to respond to people’s news.
ለሰዎች ዜና ምላሽ ለመስጠት ትክክለኛውን አማራጭ ይምረጡ።

Congratulations you completed the Quiz
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
x / y

Do you have any news? Come and tell us on our Facebook group, and we’ll respond!
አንዳች ዓይነት ዜና አለዎት? ወደፌስቡክ ገጻችን ብቅ ይበሉና ይንገሩን፤ ምላሽ እንሰጥዎታለን።

Join us for our next episode of How do I …, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቀሚ ቋንቋ ለመማርና የማዳመጥ ችሎታዎን ለማዳበር በቀጣዩ How do I…, ዝግጅት ይጠብቁን።

Session Vocabulary

 • a driving test
  የመንጃ ፈቃድ ፈተና

  the lottery
  ሎተሪ

  lost (past simple of ‘lose’)
  መጥፋት፣ ማጣት