Unit 1: How do I...
Select a unit
- 1 How do I...
- 2 Unit 2
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 8
Listen to find out how to talk about being ill.
ስለመታመም እንዴት ማውራት እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Activity 1
How do I talk about being ill?
በዛሬ ዝግጅታችን ስለመታመም እንዴት ማውራት እንደሚቻል እናያለን። ጤና ሳይሰማዎት ሲቀር ምን እንደሚሉ ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
መልስዎን ለማመሳከር ይሄንን ያዳምጡ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያመሳክሩት።

ምህረተስላሴ
እንኳን ወደ How do I… ዝግጅታችን በደህና መጡ። የማቀርብላችሁ ምህረተስላሴ ነኝ። አብራኝ ሺያን አለች።
Sian
Hi, everybody!
ምህረተስላሴ
በዚህ ዝግጅታችን ስለ ህመም 'ill' እንዴት እንደምናወራ እያለን።
የሚከተሉት ሰዎች ስለ ህመም ስሜት ሲያወሩ እናዳምጥ። ንግግራቸውን ካልተረዱት ስጋት አይግባዎት፤ ቆየት ብለን እናግዝዎታለን። ከተናጋሪዎቹ ምን ያህሉ ጤንነት እንደሚሰማቸው ለመረዳት ይሞክሩ።
I've got a cold.
I have a sore throat and a cough.
I have a headache.
ምህረተስላሴ
እሺ፤ ስለዚህ አንዳቸውም ጤናማነት እየተሰማቸው አይደለም ማለት ነው።
So, Sian, shall we look and some vocabulary to talk about being ill?
Sian
Yes, the first person said 'I've got a cold'. So if you have an illness, you can say 'I've got …' and then give the name of the illness.
ምህረተስላሴ
Yes, so 'a cold' ጉንፋን ማለት ነው። 'a' የተባለውን መስተፃምር መጨመር አይርሱ።
Sian
Yes, although if you have 'the flu', we use 'the' not 'a'. So we say 'I've got a cold' but we say 'I've got the flu'.
ምህረተስላሴ
That's right. 'Flu' ጉንፋን ነው። Now, shall we look at some of the symptoms – symptoms ምልክቶች – of a cold or the flu?
Sian
Yes, so speaker two says 'I have a cough' – and 'a cough' is this.
Let's practise the pronunciation:
a cough
I have a cough.
ምህረተስላሴ
ጉሮሯቸው 'throat' ላይ ህመም ይሰማቸዋል። ጉሮሯቸውን እንደከረከራቸው ለመግለፅ የተጠቀሙበትን ገላጭ ቅፅል ማስታወስ ይችላሉ? Let's listen again to find out.
I have a sore throat.
Sian
Yes, we use the adjective 'sore' when we feel pain. So you can have 'a sore arm' or 'a sore leg', for example. You can also use the verb 'hurt' – you can use 'hurt' with any body part where you feel pain. For example, 'my arm hurts', 'my head hurts', 'my legs hurt'.
ምህረተስላሴ
ስለዚህም 'sore' የሚከረክር የሚለውን ቅፅል ወይም የሚያም 'hurt ' የተባለውን ግስ መጠቀም ይችላሉ። ስለ አንድ የአካል ክፍል ብቻ የሚያወሩ ከሆነ መታመም የተባለውን ግስ ወደ ሶስተኛ መደብ ቅርፁ ማለትም ወደ 'hurts' እንደሚቀይሩት ያስታውሱ።
ከቀጣዩ ሰው የሰማነው ስለ ራስ ህመም ነው። Can you remember how they said this?
I have a headache.
Sian
So with some body parts we use 'ache' to say that you have a continuous pain. So you can say 'I have a…' or 'I've got a…' and then the body part and the word 'ache'.
Let's practise the pronunciation. Repeat after me:
ache
I have a headache.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ። መታመም 'ache' የተባለውን ቃል ከተለያዩ የአካል ክፍሎች ማለትም ከራስ 'head' ፣ ከጥርስ 'tooth' ፣ ከጀርባ 'back' እና ከጆሮ 'ear' ጋር መጠቀም እንችላለን።
Sian
So, if you have a pain in your ear you can say 'I have an earache'.
ምህረተስላሴ
መልካም፤ ስለ ህመም እንዴት ማውራት እንደሚቻል ተምራችኋል፤ አሁን የመለማመጃ ሰዓት ነው።
የሆድ ህመም እና ሳል እንዳለብዎት ለሐኪም የሚነገሩት እንዴት ነው? በኋላ ላይ ለንፅፅር የሺያንን መልስ ይሰማሉ።
Sian
I have a stomach ache and a cough.
ምህረተስላሴ
ተመሳሳይ ነገር ነው ያሉት? አሁን ደግሞ ለአለቃዎ ስልክ ደውለው ወደስራ እንደማይገቡ እየገለፁላቸው ነው። ጉንፋን እንደያዘዎት የሚገልፁት እንዴት ነው? የሚጠቀሙት መስተፃምር ላይ ጥንቃቄ ያድርጉ።
Sian
I've got the flu.
ምህረተስላሴ
እጅዎ ላይ ህመም ይሰማዎታል እንበል። ይሄንን የሚገልፁት እንዴት ነው? የሚያም የተሰኘውን ቅፅል ወይም መታመም የተባለውን ግስ መጠቀም ይችላሉ። ከዚያ በኋላ ሁለት አማራጭ መልሶችን ከሺያን ያዳምጣሉ።
Sian
I have a sore hand.
My hand hurts.
ምህረተስላሴ
ተመሳሳይ ነገር ነው የተናገሩት?
Sian
Well done! Hopefully you are all feeling well.
ምህረተስላሴ
Get well soon if not!
Sian
Bye, everyone!
Learn more!
1) ጉንፋን ወይንም ኢንፍሉዌንዛ ይዞኛል የምለው እንዴት ነው?
'I have...' ወይንም 'I've got...' ካሉ በኋላ የህመሙን ዓይነት ማስከተል ይችላሉ፥ ነገር ግን የሚጠቀሙት መስተፃምር ላይ ጥንቃቄ ያድርጉ።
- I've got a cold.
- I have the flu.
2) የማያቋርጥ ህመም ሲሰማዎት 'ache' የሚለውን ቃል ተጠቅመው ሊያወሩባቸው የሚችሉ የአካል ክፍሎች የትኞቹ ናቸው?
ከጥርስ 'tooth' ፥ ከራስ 'head' ፥ ከጀርባ 'back' ፥ ከጆሮ 'ear' እና ከሆድ 'stomach' ህመሞች ጋር ልንጠቀመው እንችላለን።
- I've got a stomach ache.
- I have a toothache.
ጉንፋን ወይንም ኢንፍሉዌንዛ ሲይዝ ያሉ ምልክቶችን የምንገልፀው እንዴት ነው? 'I have...' ወይንም ማለት 'I've got...' ይችላሉ።
- I've got a sore throat. (ጉሮሮዬን ይከረክረኛል)
- I've got a cough. (ያስለኛል)
- I've got a temperature. (ያተኩሰኛል)
ስለመታመም ማውራት የምችለው እንዴት ነው?
3 Questions
Choose the correct option to fill the gap.
ክፍት ቦታውን ለመሙላት ትክክለኛውን አማራጭ ይምረጡ።
Help
Activity
Choose the correct option to fill the gap.
ክፍት ቦታውን ለመሙላት ትክክለኛውን አማራጭ ይምረጡ።
Hint
ከ'cold' ጋር የምንጠቀመው መስተፃምር ያስፈልገናል።Question 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct option to fill the gap.
ክፍት ቦታውን ለመሙላት ትክክለኛውን አማራጭ ይምረጡ።
Hint
በእንግሊዝኛ የራስ ምታት የምንለው እንዴት ነው?Question 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct option to fill the gap.
ክፍት ቦታውን ለመሙላት ትክክለኛውን አማራጭ ይምረጡ።
Hint
አንድ የአካል ክፍል ላይ ህመም እንደተሰማዎት ሲናገሩ የሚጠቀሙበት ግስ ያስፈልግዎታል።Question 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Come to our Facebook group to tell us how you feel!
ወደፌስቡክ ቡድናችን ይምጡና የሚሰማዎትን ይንገሩን።
Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቀሚ ቋንቋ ለሚማሩበት እና የማዳመጥ ችሎታዎን ለሚያዳብሩብት How do I…, ዝግጅት በቀጣዩ ክፍል ይጠብቁን።
Session Vocabulary
a cold
ጉንፋንthe flu
ኢንፍሉዌንዛa cough
ሳልa sore throat
የጉሮሮ ህመምa headache
የራስ ምታትa stomach ache
የሆድ ህመምa toothache
የጥርስ ህመምan earache
የጆሮ ህመምa backache
የጀርባ ህመም