Learning English

Inspiring language learning since 1943

English Change language

Session 7

Listen to find out how to compare more than two things in English.
ሁለት ነገሮችን እንዴት ማነፃፀር እንደሚችሉ ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።

Sessions in this unit

Session 7 score

0 / 4

 • 0 / 4
  Activity 1

Activity 1

How do I compare more than two things?

በዛሬው ዝግጅታችን ስለእነዚህ ምግቦች እናወራለን።

 • Japanese food
 • Mexican food
 • Italian food
 • English food

በእርስዎ አስተያየት በጣም ጥሩ ነው ከሚሉት በጣም መጥፎ ነው ወደሚሉት በቅደም ተከተል ያስቀምጡት። ከዚያም ይሄንን ክፍል ያዳምጡና አስተያየትዎን በእንግሊዝኛ እንዴት መግለፅ እንደሚችሉ ይማሩ።

መልሶችዎችን ለመፈተሽ ይሄንን ያዳምጡ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያመሳክሩ።

Show transcript Hide transcript

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን እንኳን ወደ How do I… ዝግጅታችን በደህና መጡ። እኔ ምህረተስላሴና ሳም አብረናችሁ ነን።

Sam
Hello, everybody. Welcome!

ምህረተስላሴ
በዚህ ዝግጅታችን ከሁለት በላይ ነገሮችን እንዴት እንደምናነፃፅር እንመለከታለን። የሚከተሉት ሰዎች ስለ አንዳች ነገር አስተያየታቸውን ሲሰጡ በማዳመጥ እንጀምር። ንግግራቸው ግልፅ ካልሆነልዎት ስጋት አይግባዎት፤ በኋላ እናግዝዎታለን። ለአሁኑ ስለምን ጉዳይ እያወሩ እንደሆነ ብቻ ለመገንዘብ ይሞክሩ።

1. I think Japanese food is the nicest food in the world. It's definitely the tastiest.
2. Mexican food is the most delicious, in my opinion.
3. Of all the food in the world, Italian is the best! And English is the worst.

ምህረተስላሴ
Ah, I'm hungry now! ሲያወሩ የነበረው ስለ ምግብ ነው። አይደለም እንዴ? ስለተለያዩ የዓለም ምግቦች አስተያየታቸውን እየሰነዘሩ ነበር።

Sam
Yes, they talked about Japanese, Mexican, Italian and English food. So they were taking one type of food and comparing it to many others.

ምህረተስላሴ
ይሄንን ለማድረግ ቅፅሎችን እንጠቀማለን፤ ቀደም ሲል እንደሰማናቸው አይነት 'nice' ጥሩ፣ 'tasty' ጣፋጭ፣ 'delicious' የሚጥም፣ 'good' ጥሩ፣ 'bad' መጥፎ የመሳሰሉትን ተጠቅመን እንቀይራቸዋለን።

Sam
Let's listen again to the first speaker – how does he use the words 'nice' and 'tasty'?

I think Japanese food is the nicest food in the world. It's definitely the tastiest.

ምህረተስላሴ
ስለዚህ 'nice'ን የመሰሉ ባለ አንድ ድምፅ እና 'tasty'ን የመሰሉ ባለሁለት ድምፅ ቅፅሎችን ለመቀየር የምንጠቀመው ህግ ከፊታቸው 'the' የተባለውን ቃል ማስገባትና መጨረሻቸውን '-est' ማድረግ ነው።
'Nice' የተባለው ቃል ላይ መጨረሻው 'e' በመሆኑ የምንጨምርበት 'st'ን ብቻ ነው።

Sam
Let's quickly practise! Repeat after me:
the nicest
the tastiest

ምህረተስላሴ
'Delicious' እንደሚለው ቃልና ከሱም በላይ የሚረዝሙ ባለ ሁለት ድምጽ ቃላት ሲኖሩ ምን ይደረጋል? Listen again.

Mexican food is the most delicious, in my opinion.

Sam
In this case, we don't change the adjective – 'delicious' stays 'delicious'.

ምህረተስላሴ
ከዚያ ይልቅ ከቅፅሉ በፊት 'the most'ን እንጨምራለን።

Sam
Yes, so 'interesting' becomes 'the most interesting', 'exciting' becomes 'the most exciting', etcetera. Shall we practise the pronunciation? Repeat after me, please:
…the most delicious…
It's the most delicious food in the world.

And we just have two more to look at quickly!

ምህረተስላሴ
ካወራነው ሕግ የሚያፈነግጡ ሁለት አወቃቀሮች አሉ። እስኪ ቀጣዩን ያዳምጡና ሊለዩዋቸው ይሞክሩ። ልብ ይበሉ ይህ አወቃቀር ሁሌም 'the'ን ይይዛል።

Italian is the best! And English is the worst.

Sam
They were 'the best' and 'the worst'.

ምህረተስላሴ
እነዚህ አፈንጋጭ የሆኑበት ምክንያት ስርወ ቃላቸው 'good' እና 'bad'ን ስለማይመስሉ ነው። የእነዚህ መጨረሻ ላይ 'est' እንጨምርም።

Sam
Repeat after me:
the best
the worst

ምህረተስላሴ
እንግሊዝኛ ለመማር ርካሹ አማራጭ የቱ እንደሆነ ለማወቅ ይሞክሩ። በመፅሐፍ በመታገዝ መማር 'alone with a book'፣ ትምህርት ቤት ውስጥ 'in class' ወይስ በበይነ መረብ 'online'? መማር ይሻላል። የምትጠቀሙት ቅፅል 'cheap' ነው። ለማመሳከር መጨረሻ ላይ የሳምን መልስ ይሰማሉ።

Sam
Online is the cheapest way to learn English.

ምህረተስላሴ
አሁን ደግሞ ከሁሉም በበለጠ ማራኪ ወይም ሳቢ የሆነው የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ይሞክሩ። የምትጠቀሙት ቅፅል 'interesting' ነው። አሁንም ለማመሳከር በኋላ ላይ የሳምን መልስ ይሰማሉ።

Sam
Online with BBC Learning English is the most interesting way to learn English. Of course!

ምህረተስላሴ
Good point, Sam!

Sam
Yes, because we're the best.

ምህረተስላሴ
ለተጨማሪ የ How do I…! ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!

Sam
Bye, everyone! 

Learn more! 

1. ክሁለት የሚበልጡ ነገሮችን ተመሳሳይ ቅፅል በመጠቀም ሊያነፃፅሯቸው የሚችሉት እንዴት ነው?

ባለእንድ እና ሁለት ድምፅ ቅፅሎች ጊዜ ከፊቱ 'the' እናስቀምጥና መጨረሻው ላይ '-est'ን እንጨምራለን።

• subject + be + the (adjective + -est)
My mother's house is the cleanest house I know.

• adjective ending in 'e' + -st ('e'ን አይድገሙት።)
He's the nicest man I know.

• adjective ending in 'y' + -iest ('y' ን ወደ 'I'ይቀይሩ።)
She's the prettiest girl I know.

• adjective በአንድ አናባቢ እና አንድ ተናባቢ የሚጨርስ ቅፅል በሚኖርበት ጊዜ የመጨረሻውን ተናባቢ ይድገሙት። + -est
London's the biggest city in the UK.

ከሁለት በላይ ድምፅ ያለው ቅፅል ሲኖር ከፊቱ 'the most' እናስገባና መጨረሻው ላይ ግን ምንም አንጨምርም። ቅፅሉ ራሱም አይቀየርም።

New York is the most exciting city in the world.
Mr Smith is the most interesting teacher in the school.

2. ከዚህ ህግ የሚያፈነግጡ ይኖራሉ?

Of course! እነዚህ የተለመዱ ቅፅሎች አፈንጋጭ ናቸው። ስለዚህም ሊያስታውሷቸው ይሞክሩ።

good > the best (not 'the goodest')
bad > the worst (not 'the baddest’)
fun > the most fun (not 'the funnest')

ከሁለት የሚበልጡ ነገሮችን እንዴት ያነፃፅራሉ?

4 Questions

Choose the correct option to fill the gap.
ክፍት ቦታውን ለመሙላት ትክክለኛውን አማራጭ ይመረጥ።

Congratulations you completed the Quiz
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
x / y

Come to our Facebook group to tell us what you think 'the best' food in the world is!
ወደፌስቡክ ቡድናችን ብቅ ይበሉና በዓለም ላይ ያለው 'the best' ምግብ ምን እንደሆነ ይንገሩን።

Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ቋንቋ ለመማርና እና የማዳመጥ ክህሎትዎን ለማዳበር በቀጣዩ የ How do I… ዝግጅታችን ይጠብቁን።

Session Vocabulary

 • nice
  ጥሩ/ መልካም

  tasty
  ጣፋጭ

  delicious
  ጣፋጭ

  good
  ጥሩ

  bad
  መጥፎ

  cheap
  ርካሽ

  long
  ረዥም

  fun
  አስደሳች

  pretty
  ቆንጆ

  lovely
  ተወዳጅ

  interesting
  ማራኪ

  exciting
  ደስ የሚል/አስደሳች