Learning English

Inspiring language learning since 1943

English Change language

Session 4

Listen to find out how to talk about your habits.
ስለሚያዘወትሯቸው ተግባሮች እንዴት ማውራት እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን መሰናዶ ያዳምጡ።

Sessions in this unit

Session 4 score

0 / 3

 • 0 / 3
  Activity 1

Activity 1

How do I talk about my habits?

Listen to find out how to talk about your habits.
እንዴት ስለሚያዘወትሯቸው ተግባሮች ማውራት እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን መሰናዶ ያዳምጡ።

መልሶችዎን ለመፈተሽ ይሄንን መሰናዶ ያዳምጡ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያመሳክሩ።

Show transcript Hide transcript

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን፤ ወደ How do I… ዝግጅታችን እንኳን በሰላም መጡ። አስተናጋጃችሁ እኔ ምህረተስላሴ እና ሳም አብረናችሁ አለን።

Sian
Hi, everybody!

ምህረተስላሴ
በዚህ ክፍል ስለምናዘወትራቸው ተግባሮች የምናወራባቸውን ልዩ ልዩ መንገዶች እናያለን። ቀጥለን የምንሰማቸው ሰዎች ምን ያህል ጊዜ 'exercise' የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ሲናገሩ እናዳምጥ። ንግግራቸው ግልፅ ካልሆነልዎት ብዙም ስጋት አይግባዎት፤ ቆይተን እናግዝዎታለን። ለአሁን ከሁሉም በላቀ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርገው ማን እንደሆነ ለመረዳት ይሞክሩ።

I exercise once or twice a week.
I exercise every day.
I never exercise.
I hardly ever exercise.

ምህረተስላሴ
እሺ፤ ሁለተኛው ተናጋሪ በየቀኑ ሁለት ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ከተቀሩት ተናጋሪዎች ይበልጣሉ። So, Sian, shall we look at the language we can use to talk about habits?

Sian
Yes, so first we can see that they all used the present simple tense – so this is how we usually talk about habits.

ምህረተስላሴ
እሺ፤ ስለምናዘወትራቸው ተግባሮች ለማውራት የአሁን ጊዜ ቅርጽ ያለው አረፍተ ነገር እንጠቀማለን። አንድን ነገር ምን ያህል ጊዜ ደጋግመን እንደምናከናውነው ለመግለፅ የድግግሞሽ ግስ ገላጭን እንጠቀማለን። ተናጋሪውን በድጋሚ እናዳምጣቸው፤ የትኛውን የድግግሞሽ ግስ ገላጭ ነው የተጠቀሙት?

I never exercise.

Sian
Ok, so they use the adverb 'never' which means 'not at any time'. And the opposite of 'never' is 'always' – this means 'at all times'.

ምህረተስላሴ
የግስ ገላጩ የገባበትን ቦታ ልብ ብለዋል? በአረፍተ ነገሩ ባለቤት እና በግሱ መካከል ነው የሚገባው።

Sian
But can you remember the adverb that you heard to mean 'almost never'? Let's listen again to find out.

I hardly ever exercise.

ምህረተስላሴ
'Hardly ever'ን የምንጠቀመው ከስንት ጊዜ አንዴ ካልሆነ በስተቀር ስለማናደርገው ነገር ለማውራት ነው። Let's practise the pronunciation, Sian.

Sian
Repeat after me.
I hardly ever exercise.

ምህረተስላሴ
አንዳንዴ የሚል ትርጉም ያለውን 'sometimes' እና ብዙ ጊዜ የሚል ትርጉም የሚሰጠንን 'often'ን የመሰሉ ሌሎች የግስ ገላጮችን መጠቀም እንችላለን።

Sian
And they also go between the subject and the verb. Let's practise the pronunciation. Repeat after me.
I sometimes exercise.
I often exercise.

ምህረተስላሴ
አንድን ነገር በምን ያህል ቀን ልዩነት እንደምናከናውን መናገርም እንችላለን፤ አይደለም እንዴ?

Sian
Yes, so if you do something all the days of the week, you can use 'every day' but, careful, the position of this is different. Where does it go? Let's listen again.

I exercise every day.

ምህረተስላሴ
ስለዚህም በየቀኑ 'every day' የሚመጣው ከግስ በኋላ ነው። እንደሚከተለውም በአረፍተ ነገር መጀመሪያ ላይ ልናስገባው እንችላለን። Every day I do exercise.

Sian
But if you want to say that you do something one time or two times a week we use 'once a week' or 'twice a week'. Let's practise the pronunciation. Repeat after me.
…twice a week…
I exercise twice a week.

ምህረተስላሴ
በሳምንት ውስጥ ከአንዴ 'once' ወይንም ከሁለቴ 'twice' በላይ የምናደርገው ከሆነ ቁጥሩን እንናገርና 'times'ን እናስከትላለን።

I exercise five times a week.

ምህረተስላሴ
ስለሚያዘወትሯቸው ተግባሮች የሚናገሩባቸውን የተለያዩ መንገዶች ተምረዋል። አሁን ልምምድ ማድረጊያ ጊዜ ነው።
ጓደኛዎ እንግሊዝኛ በምን ያህል ጊዜ ልዩነት እንደሚማሩ ጠየቀዎት እንበል። በሳምንት ሶስት ቀን እንግሊዝኛ እንደሚማሩ ይንገሩት። በኋላ የሺያንን መልስ ሰምተው ከርስዎ ምላሽ ጋር ያነጻጽራሉ።

Sian
I study English three times a week.

ምህረተስላሴ
መልስዎ ተመሳሳይ ነበር? አሁን ደግሞ ጓደኛዎ ምን ያህል ጊዜ ቡና እንደሚጠጡ ጠየቀዎት እንበል። በረዥም ጊዜ አንዴ ካልሆነ በስተቀር ቡና እንደማይጠጡ ይናገሩ። የግስ ገላጩን ቦታ ያስታውሱ።

Sian
I hardly ever drink coffee.

ምህረተስላሴ
ምላሽዎ ተመሳሳይ ነበር?

Sian
Well done! Hopefully you always study English with us!

ምህረተስላሴ
And you visit our website every day! See you next time.

Sian
Bye, everyone!

Learn more! 

1) ስለምናዘወትራቸውተግባሮች በእንግሊዝኛለማውራት የምንጠቀምበት የአረፍተ ነገር አወቃቀር ምንድን ነው?

ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው ቀላል የአሁን ጊዜ አረፍተ ነገርን ነው

 •  I eat rice every day.

2) በመደበኛነት ወይም ሁልጊዜ ስለምናደርጋቸው ነገሮች ለማውራት ምን ምን የግስ ገላጮችን እንጠቀማለን?

የድግግሞሽ ግስ ገላጮችን መጠቀም እንችላለን። ብዙ ጊዜ በአረፍተ ነገሩ ባለቤት እና በግሱ መካከል ይገባሉ። 

 • I never eat fast food
 • I often read in bed.
 • I hardly ever eat chocolate.

3) አንድን ነገር በሳምንት ምን ያህል ጊዜ እንደምናደርገው የምንናገረው እንዴት ነው? 

አንድን ነገር በየቀኑ የሚያደርጉት ከሆነ 'every day' የሚለውን ሐረግ መጠቀም ይችላሉ። ይህም በአረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ወይንም መቋጫ ላይ ሊመጣ ይችላል።

 •  I have a shower every day.

ደጋግመው እንደሚያደርጉት ለመግለፅ ቁጥሩን እና አስከትሎም 'times a week' የሚለውን ሐረግ በማስገባት መናገር ይችላሉ።

በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ከሆነ የሚያደርጉት 'once a week' ይበሉ፤ ሁለት ጊዜ ከሆነ ደግሞ 'twice a week' ይላሉ፤ ሳምንትን ወደ 'month' ወር፣ ወደ 'year' ዓመት ወይም ወደ 'day' ቀን መቀየር እንደሚችሉ አይዘንጉ።

 • I play football once a week.
 • I go to the cinema three times a month.
 • I eat out twice a month.

ስለማዘወትራቸው ተግባሮች የማወራው እንዴት ነው?

3 Questions

Complete the gaps in these sentences.
በአረፍተ ነገሮቹ መካከል ያሉትን ክፍት ቦታዎች ይሙሉ።

Congratulations you completed the Quiz
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
x / y

Come to our Facebook group and tell us how often you study English.
ወደፌስቡክ ገጻችን ብቅ ይበሉና እንግሊዝኛን በሳምንት ምን ያህል ጊዜ እንደሚያጠኑ ይንገሩን።

Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ቋንቋ ለመማርና እና የማዳመጥ ክህሎትዎን ለማዳበር በቀጣዩ የ How do I… ዝግጅታችን ይጠብቁን።

Session Vocabulary

 • always
  ሁልጊዜ

  often
  ብዙ ጊዜ

  sometimes
  አንዳንዴ

  hardly ever
  ከስንት አንዴ

  never
  መቼም የማይደረግ

  once
  አን

  twice
  ሁለቴ

  three times
  ሶስት ጊዜ