Learning English

Inspiring language learning since 1943

English Change language

Session 3

Listen to find out how to give directions in English.
በእንግሊዝኛ አቅጣጫን እንዴት መጠቆም እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን መሰናዶ ያዳምጡ።

Sessions in this unit

Session 3 score

0 / 4

 • 0 / 4
  Activity 1

Activity 1

How do I give directions?

ሳይመን የገበያ መደብር ውስጥ የማያውቃቸውን ሶስት ሰዎች አቅጣጫ ሲጠይቃቸው ያዳምጡ። ለሳይመን የሚነግሩት አቅጣጫ ተመሳሳይ ነው?

መልሶችዎን ለመፈተሽ ይሄንን መሰናዶ ያዳምጡ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያመሳክሩ።

Show transcript Hide transcript

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን፤ ወደ How do I… ዝግጅታችን እንኳን በሰላም መጡ። አስተናጋጃችሁ እኔ ምህረተስላሴ እና ሳም አብረናችሁ አለን።

Sam
Hello! And welcome!

ምህረተስላሴ
ዛሬ እንዴት አቅጣጫ መጠቆም እንደምንችል እንማራለን። ሳይመን አውቶብስ መናኸሪያ ውስጥ ሶስት የማያውቃቸውን ሰዎች አቅጣጫ ሲጠይቅ እናዳምጥ። ሁሉም ነገር ግልፅ ካልሆነልዎ ብዙም አይስጉ፤ ኋላ ላይ እናግዝዎታለን። አሁን ሶስቱ ሰዎች ለሳይመን የሚነግሩት አቅጣጫ አንድ ዓይነት መሆን አለመሆኑን ይወስኑ።

Excuse me! Where's the bus station, please?
1. Go straight on, take the first road on the left, and it'll be on your right.
2. Go straight down here, take the first road on your left, and it's on the right.
3. Just go straight, turn left at the supermarket. It'll be on the right.

ምህረተስላሴ
አዳመጡ? ምንም እንኳ ተናጋሪዎቹ የተለያዩ ሐረጎች ቢጠቀሙም፤ የጠቆሙት መንገድ ተመሳሳይ ነው።

Sam
So let's look at those different phrases they used.

ምህረተስላሴ
ሁሉም ንግግራቸውን እንዴት እንደጀመሩ ደግመን እናዳምጥ እስኪ፤ በምን መልኩ ይመሳሰላሉ?

Go straight on…
Go straight down here…
…just go straight…

ምህረተስላሴ
ሶስቱም ሰዎች ቀጥ ብለህ ተጓዝ 'go straight' የሚለውን መልዕክት በተለያየ መንገድ ነግረውታል። አንደኛው 'go straight on' ሲል ሌላኛው ደግሞ 'go straight down here' ብሏል። ሁሉም የያዘውን አቅጣጫ ሳይቀይር በአንድ መንገድ እንዲሄድ ነግረውታል።

Sam
You can even say 'go straight up here'! Let's practise the pronunciation. Repeat after me:
Go straight on.
Go straight down here.

ምህረተስላሴ
በመቀጠል 'take' መያዝ የሚለውን ቃል የሚጠቀሙ ሐረጎችን እንይ። ከዚህ ግስ በኋላ ምን ይመጣል? ደግመው ያዳምጡ።

…take the first road on the left…
…take the first road on your left…

ምህረተስላሴ
እሺ፤ 'take' ን ተከትለው የመጀመሪያው መንገድ 'the first road' ወይም ሁለተኛው መንገድ 'the second road' ወዘተ. . . ይመጣሉ፤ ከነርሱ በኋላ በስተግራ 'on the left' ወይም በስተቀኝ 'on the right' ይከተላሉ።

Sam
And here, you can use 'on the' or 'on your' before 'right' and 'left'. Shall we practise? Repeat after me:
Take the first road on the right.

ምህረተስላሴ
አስከትለን መታጠፍ 'turn' የሚለው ቃል ያለባቸው ሐረጎችን እንይ። ከዚህ ግስ በኋላ ምን ይመጣል?

…turn left at the supermarket.

Sam
Left or right!

ምህረተስላሴ
Yes! እንደ ገበያ መደብር ካለ ታዋቂ ምልክት በፊት 'at'ን መጠቀም የሚችሉ ሲሆን፤ 'on'ን ደግሞ ከመንገድ ስያሜ ጋር እንጠቀመዋለን።

Sam
Quick practice! Repeat after me:
Turn left at the supermarket.

ምህረተስላሴ
በስተመጨረሻ ሰዎቹ የሳይመንን መዳረሻ እንዴት ነገሩት? ደግመው ያዳምጡ።

…and it'll be on your right.
…and it's on the right.
It'll be on the right.

Sam
They used 'on the' or 'on your' before 'right' and 'left' again. And before that?

ምህረተስላሴ
ከዚያ በፊት የ'it will be' ይሆናል አጭር ቅርፅ የሆነውን 'it'll be'ን ተጠቅመዋል፤ ወይም ደግሞ 'it's' ነው ብለዋል።

Sam
And repeat after me:
It's on the left.
It'll be on the right.

ምህረተስላሴ
አሁን ልምምድ የሚያደርጉበት ጊዜ ነው። አንድ ሰው ወደ ባንክ የሚሄድበትን አቅጣጫ ጠየቀዎት እንበል። እስኪ አንድ ላይ ሆነን አቅጣጫ እንጠቁመው፤ በኋላ ላይ የሳምን መልስ ሰምተን እናመሳክራለን። በመጀመሪያ 'on' የሚለውን ቃል በመጠቀም ቀጥ ብሎ እንዲሄድ እንንገረው።

Sam
Go straight on…

ምህረተስላሴ
Great! አሁን በስተግራ በኩል ወደ ሲኒማ ቤት 'cinema' እንዲታጠፍ እንንገረው። ከ'cinema' በፊት 'at'ን መጠቀም ያስታውሱ።

Sam
Turn left at the cinema…

ምህረተስላሴ
በመጨረሻም በስተግራ በኩል እንደሆነ ንገሩት፤ 'on the' የሚለውን መጠቀም ያስፈልግዎታል።

Sam
It's on the left.

ምህረተስላሴ
Well done! አሁን በየትኛውም ቦታ ለማንኛውም ሰው አቅጣጫ መጠቆም ችለዋል። ለሌላ የ How do I… መሰናዶ በሚቀጥለው ሳምንት ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!

Sam
See you next time! Bye, everyone! 

Learn more! 

1. አንድ ሰው በተመሳሳይ አቅጣጫ መጓዙን እንዲቀጥል የምነግረውእንዴት ነው?

አንድን ሰው ቀጥ ብሎ እንዲሄድ ለመንገር በምንፈልግበት ጊዜ 'go straight' የሚለውን ሐረግ እንጠቀማለን። ተመሳሳይ ትርጉም ከሚሰጡን ቀጣዮቹ አገላለጾች አንዱን መጠቀምም እንችላለን።

Go straight on…
Go straight down here…
Go straight up here…

2. አንድ ሰው አቅጣጫ እንዲቀይር እንዴት እንነግራለን?

ወደ ግራ ታጠፍ 'turn left' ወይም ወደ ቀኝ ታጠፍ 'turn right' ብለን መናገር እንችላለን። የሚታጠፉበትን ቦታ ለመጠቆም ስንፈልግ ለህንፃ ወይም ለታወቀ የከተማ ምልክት 'at' ን፣ ለመንገድ ወይም ለጎዳና ደግም 'on' ን እጠቀማለን።

Turn left at the cinema.
Turn right on Queen Street.

የተወሰነን መንገድ እንዲጠቀሙ 'take' ሊሏቸውም ይችላሉ።

Take the first road on the left.
Take the second road on your right.

'On the left' ወይም 'on your left'ማለት ይችላሉ፤ ነገር ግን ሁሌም 'the' ን ከ 'first'፣ 'second'፣ 'third' ወዘተ ጋር መጠቀምን ያስታውሱ።

3. አንድሰው ትክክለኛመዳረሻው ቦታ እንዴት እንነግረዋለን?

'It's' (it is) ወይንም 'it'll be' (it will be), የሚለውን ተጠቅመው 'on the/ your right/ left'ን ማስከተል ይችላሉ።

It's on the right.
It'll be on your left.

4. አቅጣጫን ለመግለፅ የምንጠቀመው የአረፍተ ነገር አወቃቀር ምንድን ነው?

ትዕዛዝ የመስጫ ወይም የአሁን ቀጥተኛ አረፍተ ነገርን አወቃቀርን እንጠቀማለን፤ ይህንንም አወቃቀር ትዕዛዝ ወይም መመሪያን ለማስተላለፍ እንጠቀምበታለን። ይህም የግሱን መሰረታዊ ቅርፅ ወስዶ የአረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ላይ ማስቀመጥ ማለት ነው።

Go straight on, take the first road on the left, turn left at the cinema.

አቅጣጫ የምጠቁመው እንዴት ነው?

4 Questions

Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀመጡ

Congratulations you completed the Quiz
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
x / y

Join our Facebook group to practise more!
ወደ ፌስቡክ ገጻችን ያምሩና ተጨማሪ ልምምድ ያድርጉ።

Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ቋንቋ ለመማርና እና የማዳመጥ ክህሎትዎን ለማዳበር በቀጣዩ የ How do I… ዝግጅታችን ይጠብቁን።

Session Vocabulary

 • left
  ግራ

  right
  ቀኝ

  the first…
  የመጀመሪያው

  the second…
  ሁለተኛው 

  road
  መንገድ 

  supermarket
  የገበያ መደብር 

  cinema
  ሲማ