Learning English

Inspiring language learning since 1943

English Change language

Session 2

Listen to find out how to ask for information in English.
መረጃ በትህትና እንዴት መጠየቅ እንደሚችሉ ለማወቅ ይሄንን መሰናዶ ያዳምጡ።

Sessions in this unit

Session 2 score

0 / 4

 • 0 / 4
  Activity 1

Activity 1

How do I ask for information politely?

የሚከተሉትን ውስን ትህትና ከተሞላ ከፍተኛ ትህትና ወዳለበት በቅደም ተከተል ያስቀመጡ

Where’s the nearest supermarket, please?
Tell me where the nearest supermarket is. 
Can you tell me where the nearest supermarket is, please?

መልስዎን ለማመሳከር ያዳምጡ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያመሳክሩት።

Show transcript Hide transcript

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ወደ How do I… ዝግጅታችን በሰላም መጡ። አስተናጋጃችሁ እኔ ምህረተስላሴ እና ሳም አብረናችሁ አለን።

Sam
Welcome, everybody.

ምህረተስላሴ
ዛሬ እንዴት መረጃ መጠየቅ እንደምንችል እናያለን፤ በአዳም እና በሌሎች ሶስት ሰዎች መካከል የተከናወኑ ሶስት አጫጭር ውይይቶችን በማዳመጥ እንጀምር። ንግግራቸው ግልፅ ካልሆነልዎት ብዙም አይስጉ፤ ቆይተን እናግዝዎታለን። ለአሁኑ አዳምን ያዳምጡትና የሚያናግራቸውን ሰዎች ያውቃቸዋል ወይስ አያውቃቸውም የሚለውን ለመረዳት ይሞክሩ። 'The nearest supermarket' በቅርብ ያለው የገበያ መደብር የሚለው ሀረግ ለግንዛቤ ይረዳዎታል።

Adam
Excuse me! Where's the nearest supermarket, please?
Woman 1
Oh, yes. Turn down here on the left, then…

Adam
Hello! Sorry to bother you. Do you know where the nearest supermarket is, please?
Man
Yes, I do. Go straight down here, then…

Adam
Hello! Can you tell me where the nearest supermarket is, please?
Woman 2
Yes, of course I can. It's just down here on the…

ምህረተስላሴ
ሳም ምን ታስቢያለሽ? አዳም የሚጠይቃቸውን ሰዎች የሚያውቃቸው ይመስልሻል?

Sam
No, I think he was talking to strangers, people he didn't know. So he was being very polite.

ምህረተስላሴ
አዎ፤ በጣም ትሁት 'polite' ነበር። ሳም፤ አዳም ሰዎቹን በትህትና ለመጠየቅ የተጠቀማቸው ቃላት እና ሐረጎች ምን ምን ናቸው?

Sam
Well, he used 'please' a lot! And also 'excuse me' and 'sorry to bother you' in a polite voice or intonation.

ምህረተስላሴ
አዎ፤ የሰዎቹን አትኩሮት በትህትና ለመሳብ እነዚህን ሐረጎች ተጠቅሟል፥ አይደለም እንዴ?

Sam
Absolutely! And then he asked for the same thing, but in three different ways.

ምህረተስላሴ
ስለዚህ የመጀመሪያውን ጥያቄ ደግመን እንስማ። ጥያቄውን እንዴት ነው የጀመረው?

Where's the nearest supermarket, please?

ምህረተስላሴ
ጥያቄውን የጀመረው 'Where's…' በማለት ነው። 'Where' እና 'is' የተባሉትን ቃላት በማጣመር የተመሰረተ ሀረግ ነው፤ ከዚያም የሚጠይቀውን ነገር አስከትሏል። 'Where' ከሚለው ቃል ውጭ ሌላ ቃል መጠቀምም ይችላሉ።

Sam
Yeah, you can say 'What's the nearest supermarket?' or 'Which is the nearest supermarket?'
Shall we practise the pronunciation? Repeat after me:
Where's the nearest supermarket, please?

ምህረተስላሴ
Thank you, Sam! የአዳም ጥያቄ በትህትና የተሞላ ቢሆንም ቀጥተኛ ነበር። ቀጥተኛ ያልሆኑ ጥያቄ ማቅረቢያ መንገዶችም አሉ። አዳምን እንደገና እናዳምጠው፤ የጥያቄው ሁለተኛ ክፍል ተመሳሳይ ነው፤ ጥያቄው እንዴት እንደሚጀምር ግን ልብ አሉ?

Do you know where the nearest supermarket is, please?
Can you tell me where the nearest supermarket is, please?

ምህረተስላሴ
እሺ፤ የመጀመሪያው ጥያቄ 'Do you know where…?' የት እንደሚገኝ ያውቃሉ? በሚል ነው የጀመረው።

Sam
And the second question started with 'Can you tell me where…?'

ምህረተስላሴ
ይህም የት እንደሚገኝ ሊነግሩኝ ይችላሉ? ማለት ነው። የሁለቱ ጥያቄዎች መደምደሚያ ምንድን ነው? አነባበቡን ሲለማመዱን ሳምን ያዳምጡ። 'Is' የተባለው ግስ የት እንደሚገባም ልብ ይበሉ።

Sam
Ready? Repeat after me:
Do you know where the nearest supermarket is, please?
Can you tell me where the nearest supermarket is, please?

ምህረተስላሴ
ልብ አሉ? በዚህኛው ምሳሌ 'is' እንደገባው፤ ቀጥተኛ ባልሆኑ ጥያቄዎች ግሶች ከሚጠይቁት ነገር በኋላ ይመጣል።
አሁን ልምምድ የሚያደርጉበት ጊዜ ነው። 'The toilet' የመፀዳጃ ቤቱ የት እንደሚገኝ ማወቅ ይፈልጋሉ እንበል፤ እናም አንድ የማያውቁትን ሰው ይጠይቁ። ጥያቄውን 'where' ብለው ይጀምሩ፤ 'please' ማለትንም አይርሱ፤ ከዚያም የሳምን ምላሽ ያዳምጡ።

Sam
Where's the toilet, please?

ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ። አሁን መፀዳጃ ቤቱ የት እንደሚገኝ በድጋሚ ይጠይቁ። አሁን ግን 'is' ን ከ 'the toilet' በኋላ ያስገቡ።

Sam
Do you know where the toilet is, please?

ምህረተስላሴ
Good! 'Can you tell me where the toilet is, please?' ማለትም ይችላሉ። አሁን እንዴት በትህትና መረጃ መጠየቅ እንደሚችሉ ተምረዋል።

Sam
Yes, well done, everyone!

ምህረተስላሴ
ለሌላ የ How do I… ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!

Sam
Until next time, bye!

Learn more! 

1. አንድን ሰው መረጃ መጠየቅ ከፈለግኩ እንዴትአትኩሮታቸውን መሳብ እችላለሁ?

የተለመዱት ሐረጋት የሚከተሉት ናቸው።

Excuse me!
Sorry!
Sorry to bother you.

2. 'Please' እና 'thank you' ካልኩ በቂ ትህትናን አሳይቻለሁ?

ቀጥተኛ ጥያቄን ‘please’ መጨረሻው ላይ አስግብተው ከትክክለኛ የአነጋገር ቅላፄ ጋር ካቀረቡት ትህትና አሳይተዋል። የቀጥተኛ ጥያቄ ቅርፅ እንደሚከተለው ነው።

Where’s the nearest supermarket, please?
Where does bus number 10 leave from, please?

የመጠየቂያ ቃል

be ግስ ወይም ረዳት ግስ

ድርጊት ተቀባይ ወይም ነገር

ዋና ግስ

 

Where

What

Which

When

How

 

 

is/ are

 

the nearest supermarket?

 

 

 

does/ do

 

bus number 10

leave from?

3. በእንግሊዝኛ ተጨማሪ በትህትና ጥያቄን የማቅረቢያ መዋቅሮች አሉ?

አዎ፤ ቀጥተኛ ያልሆነ ጥያቄን መጠየቅ ይችላሉ፤ እንደሚከተለው ዓይነት

Do you know where the nearest supermarket is, please?
Can you tell me where the nearest supermarket is, please?

4. በቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባለሆኑ ጥያቄዎች መካከል ያለው የአወቃቀር ልዩነት ምንድን ነው?

ዋነኛው የአወቃቀር ልዩነት ቀጥተኛ ላልሆኑ ጥያቄዎች በመጠየቂያ ቃላት የማንጀምር፤ ረዳት ግስም የማንጠቀም መሆኑ ነው። ከዚያ ይልቅ ‘Do you knowወይንም Can you tell meየመሳሰሉ ሐረጋትን እንጠቀማለን።

እንደሚከተለው እንተንትነው

Do you know where the nearest supermarket is, please?
Can you tell me where bus number 10 leaves from, please?

የትህትና መግለጫ ሐረግ

የመጠየቂያ ቃል

ድርጊት ተቀባይ/ ነገር

ግስ ወይንም ዋና ግስ

 

Do you know…

 

Can you tell me…

 

where

what

which

when

wow

 

 

the nearest supermarket

 

 is/ are?

bus number 10

leaves from?

መረጃ በትህትና የምጠይቀው እንዴት ነው?

4 Questions

Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

Congratulations you completed the Quiz
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
x / y

Come to our Facebook group, where you can ask us and the rest of the group for information!
ወደፌስ ቡክ ገፋችን ብቅ ብለው እኛን እንዲሁም ሌሎቹን የቡድኑን አባላት መረጃ ይጠይቁ።
Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.

ቋንቋ ለመማርና እና የማዳመጥ ክህሎትዎን ለማዳበር በቀጣዩ የ How do I… ዝግጅታችን ይጠብቁን።

Session Vocabulary

 • the nearest supermarket
  በቅርቡ ያለው የገበያ መደብር

  the toilet
  መፀዳጃ ቤቱ

  Excuse me!
  ይቅርታ ያድርጉልኝ

  Sorry!
  ይቅርታ

  Sorry to bother you.
  ስለረብሽኩዎት ይቅርታ