Unit 2: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 48
Listen to find out how to decide where to meet someone.
ከአንድ ሰው ጋር የት መገናኘት እንዳለብዎት ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Activity 1
Where should we meet?
Listen to find out how to decide where to meet someone.
ከአንድ ሰው ጋር የት መገናኘት እንዳለብዎት ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይመልሱ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን። ሁሉም የእንግሊዝኛ ተማሪ ማወቅ ያለበትን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ምህረተስላሴ እባላለሁ። በዚህ ክፍል ስለ ዕቅድ እና አንዳችን ነገር ለማከናወን ሁኔታዎችን ስለማመቻቸት እንዴት ማውራት እንደሚቻል ይማራሉ።
ክሪስ እና ፔኒ ዛሬ ለመገናኘት ወስነዋል። የት ለመገናኘት ወሰኑ? መልሱን ለማወቅ ውይይታቸውን ያዳምጡ።
Chris
Where should we meet?
Penny
Let's meet at the station!
Chris
OK! Should I meet you outside?
Penny
Yes, see you there.
ምህረተስላሴ
ውይይታቸውን ካልተረዱት አያስቡ፤ እንከፋፍለውና እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
ክሪስ ፔኒን የት መሄድ እንዳባቸው ጠየቃት። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Where should we meet?
ምህረተስላሴ
ፔኒ ጣብያው ላይ እንዲገናኙ ኃሳብ አቀረበች። 'Let's' ብላ ጀምራ ድርጊቱን አስከተለች። በዚህኛው ምሳሌ ጣብያው 'the station' ላይ ለመገናኘት 'meet at' ነው የፈለገችው። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Let's meet at the station!
ምህረተስላሴ
'Let's meet at' በማለት ሌሎች ቦታዎችን እንደ አማራጭ ማቅረብ ይችላሉ። መናፈሻው 'the park' ወይም ካፌው 'the café' ውስጥ ማለት ይችላሉ።
Let's meet at the park!
Let's meet at the café!
ምህረተስላሴ
ክሪስ እሺ፤ 'OK' በማለት መስማማቱን አሳይቷል። ከዚያም ከጣብያው ውጭ መገናኘት 'meet' ይችሉ እንደሆነ ጠይቋታል።
OK! Should I meet you outside?
ምህረተስላሴ
ጣብያው 'inside' ውስጥ ወይም ከአጠገቡ 'near to' የመገናኘት ኃሳብ ማቅረብም ይችላሉ።
Should I meet you inside the station?
Should I meet you near to the station?
ምህረተስላሴ
ፔኒ ከክሪስን ጋር ለመገናኘት ተስማማችና እዚያው አገኝሀለሁ አለች። 'There' ሲወራ የነበረውን ስፍራ ለመግለፅ ያገለግላል። 'See you there' እዛው እንገናኝ ማለት ነው።
Yes, see you there!
Yes, see you at the station!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ። አሁን ሶፊ እና ፖል የሚስማማቸው ቦታ ሲመርጡ በማዳምጥ የተማሩትን ይከልሱ። የት ለመገናኘት ወሰኑ?
Sophie
Where should we meet?
Paul
How about at the park?
Sophie
I think the café is better.
Paul
OK! Let's meet there!
ምህረተስላሴ
ፖል መናፈሻ 'park' እንገናኝ አለ። ሶፊ ግን መናፈሻው ውስጥ መገናኘት አልፈለገችም። የተሻለ ነው 'better' ብላ ያሰበችውን 'café' ካፌ ጠቆመች።
I think the café is better.
ምህረተስላሴ
ፖል እሺ፤ 'OK' በማለት መስማማቱን ገለፀ። ሶፊ የተስማሙበት ቦታ እንድታገኘው ነገራት።
OK! Let's meet there!
ምህረተስላሴ
እሺ። እስኪ ደግመን እንሞክር። እንግሊዝኛውን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Where should we meet?
Let's meet at the station!
OK! Should I meet you outside?
Yes, see you there!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ። እስኪ እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ደግመው ይበሉ።
የት እንገናኝ?
Where should we meet?
ጣብያው እንገናኛ!
Let's meet at the station!
እሺ። ከጣቢያው ውጭ ላግኝሽ?
OK! Should I meet you outside?
አዎ። እዚያው እንገናኝ።
Yes, see you there!
ምህረተስላሴ
ግሩም። ስለውጥኖችዎ እንዴት ማውራት እንደሚችሉ አውቀዋል። የት መገናኘት እንደሚፈልጉ ለክሪስ በመናገር ልምምድ ያድርጉ። 'See you there!' ማለትን አይርሱ።
Where should we meet?
OK! Should I meet you outside?
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን መልስዎን ለማመሳከር ሙሉውን ውይይት ያዳምጡ።
Chris
Where should we meet?
Penny
Let's meet at the station!
Chris
OK! Should I meet you outside?
Penny
Yes, see you there!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ። በእንግሊዝኛ የሚገናኙበትን ቦታ መምረጥ ችለዋል። ለምን ጓደኛ ፈልገው የተማሩትን አይለማመዱም? አብረውን ስለነበሩ እናመሰግናለን። ለተጨማሪ Essential English በሚቀጥለው ዝግጅታችን ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ የተማሩትን ይፈትሹ።
የት እንገናኝ?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ለጥያቄ ሲሆን የሚኖረውን የቃላት ቅደም ተከተል ያስታውሱ።Question 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ከ‘መገናኘት’ በኋላ የሚያስፈልግዎት መስተዋድድ የትኛው ነው?Question 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ከውስጥ የሚሉት እንዴት ነው?Question 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ መሰናዷችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
Where should we meet?
የት እንገናኝ?
Let’s meet at the station!
ባቡር ጣብያ እንገናኝ
Should I meet you outside?
ከጣቢያው ውጪ እንገናኝ?
I think the café is better.
ካፌው የሚሻል ይመስለኛል።
the park
መናፈሻው
the café
ካፌው
outside
ከውጭ
inside
ከውስጥ
near to
አጠገብ