Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 41
Listen to find out how to get to places.
እንዴት ወደተለያዩ ቦታዎች መሄድ እንደሚቻል ያዳምጡ።
Session 41 score
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
How can I get to…?
Listen to find out how to get to places.
እንዴት ወደተለያዩ ቦታዎች መሄድ እንደሚቻል ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምፁን ያዳምጡ እና መልመጃውን ይሞክሩ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደምናቀርብበት Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ምህረተስላሴ እባላለሁ። በዚህ ክፍል እንዴት ወደተለያዩ ቦታዎች መሄድ እንደሚቻል ስለሚጠየቅባቸው መንገዶች ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች እንዴት ወደ አውሮፕላን ማረፊያ መሄድ እንደሚችሉ ሲነጋገሩ ያዳምጡ።
Sian
How can I get to the airport?
Phil
You can go by bus or taxi.
Sian
I’m late. I need a taxi!
ምህረተስላሴ
ንግግራቸውን ካልተረዱት ብዙም አይጨነቁ፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ እንዴት ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ‘airport’ እሄዳለሁ? ስትል ጥያቄ አቅርባለች።
How can I get to the airport?
ምህረተስላሴ
ሁለተኛው ተናጋሪ በአውቶብስ ‘bus’ ወይም በታክሲ ‘taxi’ መሄድ እንደምትችል ነግሯታል።
You can go by bus or taxi.
ምህረተስላሴ
መኪና እየነዱ ‘drive’ ወይም በባቡር መሄድ ‘go by train’ እንደሚቻልም መናገር ይችላሉ።
You can drive.
You can go by train.
ምህረተስላሴ
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ‘late’ ማርፈዷን ልብ አለች። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I’m late.
ምህረተስላሴ
እናም ‘taxi’ ታክሲ እንደምትፈልግ ‘need’ ተናገረች። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I need a taxi!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሰዎች ወደተለያዩ ቦታዎች እንዴት መሄድ እንደሚችሉ ሲጠያየቁ በማዳመጥ እርስዎ ካሉት ጋር ያነጻጽሩ።
ቬራ ተራራማ አካባቢ የሚኖሩ ጓደኞቿን ልትጠየቅ ነው። ለመሄድ የወሰነችው በአውሮፕላን ‘plane’ ነው።
How can I get to the mountains?
You can go by bus or plane.
I don’t have time. I want to go by plane!
ሮበርት በቅርብ ርቀት ወዳለችው ከተማ ‘next town’ መሄድ ይፈልጋል። መኪና ማግኘት ስላልቻለ በባቡር “train” ለመሄድ ወስኗል።
How can I get to the next town?
You can go by train or drive.
I don’t have a car, I want to go by train.
ምህረተስላሴ
እሺ፤ አሁን ንግግሩን ደግመን እንሞክረው። የእንግሊዝኛውን አረፍተ ነገሮች ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
How can I get to the airport?
How can I get to the airport?
You can go by bus or taxi.
You can go by bus or taxi.
I’m late.
I’m late.
I need a taxi!
I need a taxi!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ ትርጉማቸውን ይበሉ።
ወደአውሮፕላን ማረፊያው እንዴት መሄድ እችላለሁ?
How can I get to the airport?
በአውቶብስ ወይንም በታክሲ መሄድ ትችያለሽ
You can go by bus or taxi.
ረፍዶብኛል
I’m late.
ታክሲ ያስፈልገኛል!
I need a taxi!
ምህረተስላሴ
በጣም ግሩም፤ እንዴት ወደተለያዩ ቦታዎች መሄድ እንደሚቻል መጠየቅና መመለስ ተምረዋል። እንዴት ወደ አውሮፕላን ማረፊያ መሄድ እንደሚቻል ለምትጠይቀው የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ምላሽ በመስጠት ይለማመዱ።
How can I get to the airport?
I’m late. I need a taxi!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ጠቅላላውን ውይይት አንዴ ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Sian
How can I get to the airport?
Phil
You can go by bus or taxi.
Sian
I’m late. I need a taxi!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን እንዴት ወደተለያዩ ቦታዎች መሄድ እንደሚቻል በእንግሊዝኛ መጠየቅና መልስ መስጠት ችለዋል። የተማሩትን መለማመድ አይዘንጉ። ጓደኛ ይፈልጉና እንዴት ወደተለያዩ አካባቢዎች መሄድ እንደሚቻል በእንግሊዝኛ በመጠየቅ ልምምድ ያድርጉ። ለተጨማሪ የኢንሴንሻል ኢንግሊሽ መሰናዶ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
እንዴት መሄድ እችላለሁ?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
ለጥያቄዎች የምንጠቀምበትን የቃላት ቅደም ተከተል ያስታውሱ።Question 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
ለአረፍተ ነገሮች የምንጠቀምበትን የቃላት ቅደም ተከተል ያስታውሱ።Question 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
ታክሲ በሚፈልገው ሰው ይጀምሩ።Question 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ ክፍላችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
How can I go/ get to ______?
እንዴት ወደ (አንድ ቦታ) መሄድ እችላለሁ?
You can go ______.
በ ______ መሄድ ይችላሉ?
I want to go______.
በ ______ መሄድ እፈልጋለሁ።
the airport
አውሮፕላን ማረፊያ
the next town
ቀጥሎ ያለው ከተማ
by bus
በአውቶብስ
by taxi
በታክሲ
by train
በባቡር