Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 37
Listen to find out how to ask people how often they do an activity.
ሰዎች አንድ ተግባርን ምን ያህል ጊዜ እንደሚያከናውኑ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Session 37 score
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
How often do you play football?
Listen to find out how to ask people how often they do an activity.
ሰዎች አንድን ተግባር ምን ያህል ጊዜ እንደሚያከናውኑት እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምፁን ያዳምጡ እና መልመጃውን ይሞክሩ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ማወቅ የሚገባውን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ምህረተስላሴ እባላለሁ። በዚህ ክፍል ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ አንዳንድ ነገሮችን በምን ያህል ድግምግሞሽ እንደሚያደርጉ መናገርን ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች ነግሮችን ምን ያህል ደጋግመው እንደሚያደርጉ ሲነጋገሩ እናዳምጥ።
Lisa
How often do you play football?
David
I play football once a week. How about you?
Lisa
About twice a week.
ምህረተስላሴ
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ ሊሳ ዴቪድን ‘How often do you…?’ አለችና ‘play football’ ን በማስከተል እግር ኳስን ምን ያህል ደጋግሞ እንደሚጫወት ጠየቀችው። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
How often do you play football?
ምህረተስላሴ
ከዚያ ዴቪድ “በሳምንት አንዴ እግር ኳስ እጫወታለሁ” ‘I play football once a week’ ብሎ መለሰላት። በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚጫወቱ ከሆነ ‘twice’ ን መጠቀም ይችላሉ። ሦስት እና ከዚያ በላይ የሚጫወቱ ከሆነ ደግሞ ቁጥሩን እና ‘times’ የተባለውን ቃል አንድ ላይ በማድረግ መግለፅ ይችላሉ። ለምሳሌ ‘five times’ አምስት ጊዜ ማለት ነው። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I play football once a week.
ምህረተስላሴ
ከዚያም ዴቪድ ‘How about you?’ በማለት ተመሳሳይ ጥያቄ መልሶ አቅርቦላታል። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
How about you?
ምህረተስላሴ
ሊሳ በሳምንት ሁለት ጊዜ ገደማ እንደምትሮጥ መለሰችለት። ‘About’ የሚለውን ቃል የምንጠቀመው የተግባሩን አንጻራዊ መጠን ለመግለፅ ነው። ሳምንት ‘week’ የሚለውን ቃል ወደ ቀን ‘day’ ወይም ወደ ወር ‘month’ አልያም ወደ ዓመት ‘year’ መቀየር ይችላሉ። እናም ‘once a day’ ‘once a month’ ወይም ‘once a year.’ ማለት ይችላሉ። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
About twice a week.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሰዎች ነገሮችን ምን ያህል ጊዜ እንደሚያደርጉ ሲጠያየቁ በማዳመጥ እርስዎ ካሉት ጋር ያመሳክሩ።
How often do you play tennis?
I play tennis twice a month. How about you?
About three times a month.
How often do you play basketball?
I play basketball twice a week. How about you?
About twice a year.
ምህረተስላሴ
እሺ፤ አሁን ያንን ደግመን እንሞክረው። የእንግሊዝኛውን አረፍተ ነገር ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
How often do you play football?
How often do you play football?
I play football once a week.
I play football once a week.
How about you?
How about you?
About twice a week.
About twice a week.
ምህረተስላሴ
ግሩም፤ አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ምን ያህል ደጋግመህ እግር ኳስ ትጫወታለህ?
How often do you play football?
እግር ኳስ በሳምንት አንዴ እጫወታለሁ
I play football once a week.
አንቺስ?
How about you?
በሳምንት ሁለት ጊዜ አካባቢ
About twice a week.
ምህረተስላሴ
በጣም ግሩም፥ አሁን ሰዎች ነገሮችን ምን ያህል ደጋግመው እንደሚያደርጓቸው መጠየቅ አውቀዋል። ለሊሳ ምላሽ በመስጠት ልምምድ ያድርጉ። ‘How about you?’ በማለት ተከታይ ጥያቄ ማቅረብ አይዘንጉ።
How often do you play football?
About twice a week.
ምህረተስላሴ
አሁን ሙሉውን ንግግር ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Lisa
How often do you play football?
David
I play football once a week. How about you?
Lisa
About twice a week.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሰዎች ነገሮችን ምን ያህል ደጋገምው እንደሚያደርጉ በእንግሊዝኛ መጠየቅ ችለዋል። አጋር ይፈልጉና ነገሮችን ምን ያህል ደጋገመው እንደሚያደርጉ በእንግሊዝኛ በመጠየቅ ይለማመዱ። ለተጨማሪ የኢሴንሻል ኢንግሊሽ መሰናዶ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። Bye!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
ምን ያህል ጊዜ እግር ኳስ ትጫወታለህ/ቻለሽ?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ከጥያቄ ጋር ይህንን ቃል ሁሌ ከ how በኋላ እንጠቀመዋለንQuestion 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ሁሌም ይህንን ቃል በonce እና በweek መካከል እንጠቀመዋለንQuestion 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
'Once', 'twice', 'three' ______ እንላለን። ይሄ ቃል ሁሌም በ 's' ነው የሚያልቀው።Question 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በልምምድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
How often do you ______ ______?
ምን ያህል ጊዜ ______ ታደርጋለህ?I ______ ______ once a week.
በሳምንት አንዴ ______ አደርጋለሁAbout twice a week.
በሳምንት ሁለቴ አካባቢAbout twice a month.
በወር ሁለት ጊዜ አካባቢAbout three times a month.
በወር ሦስት ጊዜ ገደማAbout twice a year.
በዓመት ሁለት ጊዜ አካባቢplay football
እግር ኳስ መጫወትplay tennis
ቴኒስ መጫወትplay basketball
ቅርጫት ኳስ መጫወት