Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 34
Listen to find out how to ask what time it is.
ስንት ሰዓት እንደሆነ መጠየቅን ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Session 34 score
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
What time is it?
Listen to find out how to ask what time it is.
ስንት ሰዓት እንደሆነ መጠየቅን ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምፁን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation በደህና መጡ። ዘሩባቤል እባላለሁ። በዚህ ክፍል ሰዓት ስንት እንደሆነ ‘what time’ መጠየቅን ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች ስንት ሰዓት እንደሆነ ሲነጋገሩ ያዳምጡ።
Sian
Hi Phil, what time is it?
Phil
It’s eight forty five.
Sian
Aaargh, I start work at ten to nine…I’m late! Bye!
Phil
Bye!
ዘሩባቤል
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ ሺያን ፊልን ‘what time’ ስንት ሰዓት እንደሆነ ጠየቀችው። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
What time is it?
ዘሩባቤል
ፊል ሁለት ሰዓት ከአርባ አምስት ‘eight forty five’ መሆኑን ተናገረ። ሰዓቱን ‘eight’ ሁለት ከዚያም ደቂቃውን በመጨመር ‘forty five’ አርባ አምስት መናገር እንችላለን። ‘Eight forty five’ ሁለት ከአርባ አምስት። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
It’s eight forty five.
ዘሩባቤል
ሻን መጨነቋን ለማሳየት ‘aaargh’ አለች። ከዚያም ‘start work’ ስራ የምትጀምረው ‘ten to nine’ ለሶስት አስር ጉዳይ ላይ መሆኑን ተናገረች። ከቀጣዩ ሰዓት በፊት ከሰላሳ ያነሱ ደቂቃዎች ካሉ፥ ሰዓቱን ለመሙላት ምን ያህል ደቂቃዎች እንደሚቀሩ በመጥቀስ መናገር እንችላለን። አስር ‘ten’፤ ለ ‘to’ ከዚያ ሰዓቱ ‘nine’ ሶስት፤ ‘ten to nine’ ለሶስት አስር ጉዳይ። ‘ten to nine’ ለሶስት አስር ጉዳይ፤ ‘eight fifty’ ሁለት ሰዓት ከሃምሳ ከማለት ጋር አንድ ዓይነት ነው። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
Aaargh, I start work at ten to nine.
ዘሩባቤል
ከዚያም ሻን ‘late’ ማርፈዷን ተናግራ ‘bye’ ደህና ሁን አለች። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
I’m late! Bye!
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፥ አሁን የተለያዩ ሰዎች ስንት ሰዓት እንደሆነ ሲነጋገሩ በማዳመጥ እርስዎ ካሉት ጋር ያመሳክሩ።
አሁን ለሰባት ሰአት ሃያ ጉዳይ ነው፤ ‘twenty to one’ እና ኬቨን ‘lunch’ ለምሳ ‘late’ ረፍዶበታል።
Hi Kevin, what time is it?
It’s twenty to one.
I usually have lunch at twelve, I’m late!
ሁለት ከሃያ ነው እናም ጌሪ ‘early’ ቀድሞ ነው ‘work’ ስራ የገባው።
Hi Rachel, what time is it?
It’s eight twenty.
I start work at nine o’clock, I’m early!
ዘሩባቤል
እሺ፤ አሁን ያንን ደግመን እንሞከረው። የእንግሊዝኛውን አረፍተ ነገር ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
What time is it?
What time is it?
It’s eight forty five.
It’s eight forty five.
I start work at ten to nine.
I start work at ten to nine.
I’m late! Bye!
I’m late! Bye!
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ስንት ሰዓት ነው።
What time is it?
ለሶስት ሩብ ጉዳይ ነው።
It’s eight forty five.
ስራ የምጀምረው ለሶስት አስር ጉዳይ ላይ ነው።
I start work at ten to nine.
አርፍጃለሁ፥ ደህና ሁን
I’m late! Bye!
ዘሩባቤል
በጣም ግሩም፥ አሁን ስንት ሰዓት እንደሆነ መጠየቅ እና መናገርን አውቀዋል። ለሻን ምላሽ በመስጠት እና ሰዎች እነዚህን ነገሮች ስንት ሰዓት ላይ እንደሚያከናውኑ በመጠየቅ ልምምድ ያድርጉ።
What time is it?
ዘሩባቤል
አሁን ሙሉውን ንግግር ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Sian
Hi Phil, what time is it?
Phil
It’s eight forty five.
Sian
Aaargh, I start work at ten to nine...I’m late! Bye!
Phil
Bye!
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን ስንት ሰዓት እንደሆነ በእንግሊዝኛ መጠየቅ እና መናገርን ችለዋል። የተማሩንትን መለማመድ አይርሱ። ጓደኛ ይፈልጉና ስንት ሰዓት እንደሆነ በእንግሊዝኛ በመጠየቅ ይለማመዱ። ለተጨማሪ Essential English Conversation መሰናዶ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን።
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
ሰዓት ክንደይ እሎ?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
ጥያቄ ሲሆን የቃላቱን ቅደም ተከተል ማቀያየር አይርሱQuestion 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
ከ “to”. በፊት 5፥ 10፥ 20፥ 25 መጠቀም እንችላለንQuestion 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
Hint
ከሰዓቱ በኋላ ከ10 የሚበልጥ ደቂቃን መጥቀስ እንችላለንQuestion 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያንን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
What time is it?
ስንት ሰዓት ነው?It’s ______.
______ ነውI start work at ______.
የምጀምረው ______ ነውI usually have lunch at ______.
ብዙ ጊዜ ምሳ የምበላው ______ ላይ ነው።I’m early!
ቀድሜያለሁI’m late!
ዘግይቻለሁeight forty five
ለሶስት እሩብ ጉዳይten to nine
ለሶስት አስር ጉዳይtwenty to one
ለሰባት ሃያ ጉዳይtwelve
ስድስትeight twenty
ሁለት ከሃያnine o’clock
ሶስት ሰዓት