Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 32
Listen to find out how to ask someone what time they start work.
ሰዎች ስንት ሰዓት ላይ ስራ እንደሚጀምሩ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Session 32 score
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
What time do you start work?
Listen to find out how to ask someone what time they start work.
ሰዎች ስንት ሰዓት ላይ ስራ እንደሚጀምሩ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እንከወን በደህና መጡ። ዘሩባቤል እባላለሁ። በዚህ ክፍል ስንት ሰዓት ላይ ስራ እንደሚጀመር ‘start work’ እና ስንት ሰዓት ላይ ስራ እንደሚጨረስ ‘finish work’ መናገርን ይማርሉ።
ሁለት ሰዎች ስንት ሰዓት ላይ ስራ እንደሚጀምሩ ሲያወሩ ያዳምጡ።
Judy
Hi Paul, when do you start work?
Paul
I start work at seven thirty.
Judy
What time do you finish work?
Paul
I finish work at five thirty.
ዘሩባቤል
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ ጁዲ ፖልን ስንት ሰዓት ላይ ስራ እንደሚጀምር ‘starts work’ ጠየቀችው። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
When do you start work?
ዘሩባቤል
ፖል ስራ የሚጀምረው ‘seven thirty’ አንድ ተኩል ላይ መሆኑን ተናገረ። ‘Thirty’ ተኩልን የምንጠቀመው ከሰዓቱ በኋላ ምን ያህል ደቂቃ እንዳለ ለመጠቆም ነው። ከአንድ ሰዓት በኋላ ሰላሳ ደቂቃ አልፎ ማለት ነው። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I start work at seven thirty.
ዘሩባቤል
ከዚያም ጁዲ ፖልን ስንት ሰዓት ላይ ስራ እንደሚጨርስ ‘finishes work’ ጠየቀችው። ስለጊዜዎች ለመጠየቅ ‘when’ ወይንም ‘what time’ መጠቀም እንችላለን። ምንም ዓይነት ልዩነት የላቸውም። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
What time do you finish work?
ዘሩባቤል
ፖል ስራ የሚጨርሰው ‘five thirty’ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ እንደሆነ ተናግሯል። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I finish work at five thirty.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ የተለያዩ ሰዎች ስንት ሰዓት ላይ ስራ እንደሚጀመሩ እና እንደሚጨርሱ ሲነጋግሩ ያዳምጡና እርስዎ ያሉትን ይፈትሹ።
ራየን ስራ የሚጀምረው ሶስት ተኩል ላይ ሲሆን የሚጨርሰው ደግሞ አስር ተኩል ላይ ነው።
Hi Ryan, what time do you start work?
I start work at nine thirty.
Ok. What time do you finish work?
I finish work at four thirty.
ዘሩባቤል
ሊዝ ስራ የምትጀምረው ሶስት ተኩል ላይ ሲሆን የምትጨርሰው ደግሞ አንድ ተኩል ላይ ነው።
Hi Liz, when do you start work?
I start work at nine thirty.
OK. When do you finish work?
I finish at seven thirty.
ዘሩባቤል
እሽ፥ አሁን ደግመን እንሞክር። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ይሰማሉ።
When do you start work?
When do you start work?
I start work at seven thirty.
I start work at seven thirty.
What time do you finish work?
What time do you finish work?
I finish work at five thirty.
I finish work at five thirty.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታውሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡ እና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ስንት ሰአት ላይ ነው ስራ የምትጀምረው?
When do you start work?
ስራ የምጀምረው አንድ ተኩል ላይ ነው።
I start work at seven thirty.
ስራ የምትጨርሰው ስንት ሰዓት ላይ ነው?
What time do you finish work?
ስራ የምጨርሰው አስራ አንድ ተኩል ላይ ነው።
I finish work at five thirty.
ዘሩባቤል
በጣም ግሩም፥ አንድ ሰው ስራ የሚጀመረው እና የሚጨርሰው ስንት ሰዓት ላይ እንደሆነ መጠየቅን እና መናገርን አውቀዋል። ለጁዲ ምላሽ በመስጠት እና እነዚህን ነገሮች የምታከናውነው ስንት ሰዓት ላይ እንደሆነ በመጠየቅ ልምምድ ያድርጉ።
When do you start work?
What time do you finish work?
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን ጠቅላላውን ንግግር ያዳምጡና መልስዎን ይፈትሹ።
Judy
Hi Paul, when do you start work?
Paul
I start work at seven thirty.
Judy
What time do you finish work?
Paul
I finish work at five thirty.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! አሁን በእንግሊዝኛ ስራ ስንት ሰዓት ላይ እንደሚጀመር እና እንደሚጨርስ መጠየቅም መናገርም ይችላሉ። የተማሩትን መለማመድ ያስታውሱ። ጓደኛ ይፈልጉና ስራ ስንት ሰዓት ላይ እንደሚጀምሩ እንዲሁም እንደሚጨርሱ በእንግሊዝኛ መጠየቅን እና መናገርን ይለማመዱ። ለተጨማሪ Essential English Conversation ዝግጅቶች በቀጣይ ክፍላችችን ይጠብቁን። Bye!
Check what you’ve learned by putting the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው በማስቀመጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
ስራ ስንት ሰዓት ላይ ነው የምትጅምረው/ሪው?
3 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
Help
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
Hint
ይህ ጥያቄ አንድ ሰው ስንት ሰዓት ላይ ስራ እንደሚጀምር ለመጠየቅ ነው።Question 1 of 3
Help
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
Hint
ይህ ሰው ስራ የሚጀምርበትን ሰዓት ነው የሚናገረው።Question 2 of 3
Help
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
Hint
ይህ ሰው አንድን ሰው ስንት ሰዓት ላይ ስራ እንደሚጨርስ ነው የሚጠይቀው።Question 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Join us for our next episode of Essential English to learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያንን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
When do you start work?
ስራ የምትጀምረው ስንት ሰዓት ላይ ነው?
I start work at ______.
ስራ የምጀምረው በ ______ ሰዓት ነው።
What time do you finish work?
ስራ የምትጨርሰው ስንት ሰዓት ላይ ነው።
I finish work at ______.
ስራ የምጨርሰው ______ ላይ ነው።
five thirty
አስራ አንድ ተኩል
seven thirty
አንድ ተኩል