Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 31
Listen to find out how to ask someone what time they get up.
አንድ ሰው ስንት ሰዓት ላይ ከአልጋ እንደሚነሳ ለመጠየቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Session 31 score
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
ስንት ሰዓት ላይ ነው ከእንቅልፍ የሚነሱት?
Listen to find out how to ask someone what time they get up.
አንድ ሰው ስንት ሰዓት ላይ ከአልጋ እንደሚነሳ ለመጠየቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቀቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation በደህና መጡ። ዘሩባቤል እባላለሁ። በዚህ ክፍል መቼ ከአልጋ እንደሚነሱ 'get up' እና መቼ እንቅልፍ እንደሚተኙ 'go to bed' መናገርን ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች መቼ ከእንቅልፍ ነቅተው ከአልጋ ላይ እንደሚነሱ ሲያወሩ ያዳምጡ።
Sian
Hi Phil, when do you get up?
Phil
I get up at six o’clock.
Sian
What time do you go to bed?
Phil
I go to bed at ten o’clock.
ዘሩባቤል
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ ሻን ፊልን መቼ እንደሚነሳ ‘gets up’ ጠየቀችው።
When do you get up?
ዘሩባቤል
ፊል ‘six o’clock’ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ እንደሚነሳ ተናገረ። ሰዓቱን ለመግለፅ ቁጥሩን ከተናገርን በኋላ ‘o’clock’ እንጠቀማለን። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
I get up at six o’clock.
ዘሩባቤል
ከዚያም ሻን መቼ እንደሚተኛ ‘go to bed’ ጠየቀችው። ስለጊዜ ለመጠየቅ ‘when’ ወይንም ‘what time’ መጠቀም እንችላለን። በሁለቱ መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
What time do you go to bed?
ዘሩባቤል
ፊል ‘ten o’clock’ አራት ሰዓት ላይ እንደሚተኛ ነገራት። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I go to bed at ten o’clock.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፥ አሁን የተለያዩ ሰዎች መቼ እንደሚተኙ እና መቼ እንደሚነሱ ሲነጋገሩ በማዳመጥ እርስዎ ካሉት ጋር ያመሳክሩ።
ጆሴፍ የሚነሳው አስራ ሁለት ሰዓት ላይ ሲሆን የሚተኛው ደግሞ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ ነው።
Hi Joseph, what time do you get up?
I get up at six o’clock.
What time do you go to bed?
I go to bed at one o’clock.
ዘሩባቤል
እሽ፤ አሁን የቅድሙን ደግመን እንሞከረው። የእንግሊዝኛውን አረፍተ ነገር ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
When do you get up?
When do you get up?
I get up at six o’clock.
I get up at six o’clock.
What time do you go to bed?
What time do you go to bed?
I go to bed at ten o’clock.
I go to bed at ten o’clock.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
መቼ ነው የሚነሱት?
When do you get up?
አስራ ሁለት ሰዓት ላይ ነው የምነሳው።
I get up at six o’clock.
ስንት ሰዓት ላይ ነው የምትተኛው?
What time do you go to bed?
አራት ሰዓት ላይ ነው የምተኛው።
I go to bed at ten o’clock.
ዘሩባቤል
በጣም ግሩም፥ አሁን ስለሚተኙበት እና ስለሚነሱበት ሰዓት መጠየቅ እና መናገርን አውቀዋል። ለሻን ምላሽ በመስጠት እና እነዚህ ነገሮች ሰዎች ስንት ሰዓት ላይ እንደሚያከናውኑ በመጠየቅ ልምምድ ያድርጉ።
When do you get up?
What time do you go to bed?
ዘሩባቤል
አሁን ሙሉውን ንግግር ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Sian
Hi Phil, when do you get up?
Phil
I get up at six o’clock.
Sian
What time do you go to bed?
Phil
I go to bed at ten o’clock.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሰዎች ስንት ሰዓት ላይ እንደሚተኙ እና እንደሚነሱ በእንግሊዝኛ መጠየቅን ችለዋል። ጓደኛ ይፈልጉና ስንት ሰዓት ላይ እንደሚተኙ እና እንደሚነሱ በእንግሊዝኛ በመጠየቅ ይለማመዱ። ለተጨማሪ ጠቃሚ የእንግሊዝኛ ንግግሮች በሚቀጥለው መሰናዶ ይጠብቁን።
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
What time do you get up?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይመረጡ።
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይመረጡ።
Hint
ለመነሳት የምንጠቀምበት ቃል ምንድን ነው?Question 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይመረጡ።
Hint
ወደአልጋ ለመሄድ የምንጠቀምበት ቃል ምንድን ነው?Question 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይመረጡ።
Hint
ስለጊዜዎች ለመጠየቅ የምንጠቀምበት ቃል ምንድን ነው?Question 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Join us for our next episode of Essential English to learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያንን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
When do you get up?
ስንት ሰዓት ላይ ትነሳለህ/ሽ?
I get up at ______ o’clock.
የምነሳው ______ ሰዓት ላይ ነው ።
What time do you go to bed?
ወደአልጋ የምትሄደው/ጂው ስንት ሰዓት ላይ ነው?
I go to bed at ______ o’clock.
ወደአልጋ የምሄደው በ ______ ነው።