Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 28
Listen to find out how to ask if something is on sale in a clothing store.
በአልባሳት መደብር ውስጥ አንድ ዕቃ ቅናሽ ተደርጎበት የሚሸጥ መሆኑን እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Session 28 score
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
Is this on sale?
Listen to find out how to ask if something is on sale in a clothing store.
በአልባሳት መደብር ውስጥ አንድ ዕቃ ቅናሽ ተደርጎበት የሚሸጥ መሆኑን እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እነኳን በደህና መጡ። ዘሩባቤል እባላለሁ። በዚህ ክፍል ሱቅ ገብተው ቅናሽ የተደረገብት ዕቃ የትኛው እንደሆነ ስለመጠየቅ ይማራሉ።
ሁለቱ ሰዎች ሱቅ ውስጥ ሲነጋገሩ ያዳምጡ።
Shop assistant
Can I help you?
Phil
Yes, is this on sale?
Shop assistant
Yes, the sale price is £23.00.
Phil
Great, I’ll take it!
ዘሩባቤል
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ የሱቁ ረዳት ፊልን “ምን ልርዳህ” ‘Can I help you?’ ስትል ጠየቀችው። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
Can I help you?
ዘሩባቤል
በመቀጠል ፊል “ይህ ነገር በቅናሽ የሚሸጥ ነው?” ‘Is this on sale?’ አለ። በርከት ስላሉ ዕቃዎች መጠየቅ ከፈለጉ ‘Is this on sale?’ ማለትም ትተው “እነዚህ ነገሮች በቅናሽ የሚሸጡ ናቸው?” ‘Are these on sale?’ ይላሉ። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Yes, is this on sale?
ዘሩባቤል
ከዚያ የሱቁ ረዳት “አዎ የመሸጫ ዋጋው” ብላ ዋጋውን አስከተለች።
Yes, the sale price is £23.00.
ዘሩባቤል
ፊል ሊገዛው ፈልጎ ነበርና “በጣም ጥሩ እወስደዋለሁ” ‘Great, I’ll take it.’ አለ። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Great, I’ll take it.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች ሱቅ ውስጥ ሲነጋገሩ በማዳመጥ ከእርስዎ መልስ ጋር ያመሳክሩ።
Can I help you?
Yes, are these shoes on sale?
Yes, the sale price is £39.99.
Great, I’ll take them!
Can I help you?
Yes, is this belt on sale?
Yes, the sale price is £49.99.
Great, I’ll take it!
ዘሩባቤል
እሽ፥ ደግመን እንሞክር። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። አሁን እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጣሉ።
Can I help you?
Can I help you?
Yes, is this on sale?
Yes, is this on sale?
Yes, the sale price is £23.00.
Yes, the sale price is £23.00.
Great, I’ll take it!
Great, I’ll take it!
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታውሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ምን ልረዳዎት እችላለሁ?
Can I help you?
አዎ ይህ ቅናሽ ተደርጎበታል?
Yes, is this on sale?
አዎ የቅናሽ ዋጋው 23 ፓውንድ ነው።
Yes, the sale price is £23.00.
በጣም ጥሩ! እወስደዋለሁ።
Great, I’ll take it!
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሱቅ ውስጥ ያለ አንድ ዕቃ ቅናሽ ተደርጎበተ እንደሆነ መጠየቅ ችለዋል። ጃኬቱ በቅናሽ የሚሸጥ እንደሆነ ለሱቁ ረዳት ጥያቄ ያቅርቡ።
Can I help you?
Yes, the sale price is £23.00.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን ጠቅላላውን ንግግር ደግመው ያዳምጡ እና መልስዎን ያመሳክሩ።
Shop assistant
Can I help you?
Phil
Yes, is this on sale?
Shop assistant
Yes, the sale price is £23.00.
Phil
Great, I’ll take it!
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! አሁን ሸመታ ላይ ሲሆኑ አንድ ዕቃ በቅናሽ የሚሸጥ መሆኑን መጠየቅ ችለዋል። የተማሩትን መለማመድ አይዘንጉ። ጓደኛ ይፈልጉና ‘Is this on sale?’ የሚለውን ጥያቄ በመጠየቅ ይለማመዱ። ለተጨማሪ የ Essential English Conversation ክፍሎች በሚቀጥለው ዝግጅታችን ይጠብቁን። Bye!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
በቅናሽ የሚሸጥ ነው?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
አንድ ነገር በቅናሽ እየተሸጠ መሆኑን የሚያመላክተውን ትክክለኛውን ሐረግ ያስታውሱ።Question 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
የእነዚህ ቃላት ጥምረት የአንድን ነገር ዋጋ ለመግለፅ የሚጠቅም ነው።Question 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
አንድን ነገር እንደሚገዙ ለማሳወቅ የ‘I’ እና የዚህን ቃል ጥምረት እንጠቀማለን። ቃሉ ብዙ ጊዜ ወደፊት የሚሆንን ክስትት የሚያመላክት ነው።Question 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያንን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
Can I help you?
ምን ልረዳዎት እችላለሁ?
Yes, is this on sale?
ይሄ ነገር በቅናሽ የሚሸጥ ነው እንዴ?
Yes, is this ______ on sale?
አዎ ይህ ______ በቅናሽ የሚሸጥ ነው።
Yes, are these ______ on sale?
አዎ እነዚህ ______ በቅናሽ የሚሸጡ ናቸው።
Yes, the sale price is £______.
አዎ የቅናሽ ዋጋው ______ ፓውንድ ነው።
Great, I’ll take it!
በጣም ጥሩ፥ እወስደዋለሁ።
Great, I’ll take them!
በጣም ጥሩ፥ እወስዳቸዋለሁ።