Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 17
Listen to find out how to ask if some place is nearby.
የተለያዩ ቦታዎች በቅርብ ስለመገኘታቸው እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይህንን ያዳምጡ።
Session 17 score
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
Is there a… near here?
Listen to find out how to ask if some place is nearby.
የተለያዩ ቦታዎች በቅርብ ስለመገኘታቸው እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይህንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊተዋቸው የማይቻላቸውን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation በደህና መጡ። ምህረትእባላለሁ።በዚህ ክፍል በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ የተለያዩ ቦታዎች የት እንደሚገኙ መጠየቅን ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች በአቅራቢያቸው ምግብ ቤት ስለመኖሩ ሲነጋገሩ ያዳምጡ።
Sian
Is there a restaurant near here?
Phil
Yes, there is. It’s on Station Road.
Sian
Thanks!
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ‘ከዚህ አጠገብ’ ‘near here’ ‘ምግብ ቤት’ ‘restaurant’ መኖሩን ነው የጠየቀችው። መኖር ያለመኖሩን ለመጠየቅ ‘አለ ወይ’ ‘is there’ የሚለውን መጠየቂያ ተጠቅማለች። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
Is there a restaurant near here?
ይሄንን ጥያቄ በአቅራቢያዎ ያለ ማንኛውንም ስፍራ ለማጠያየቅ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። እነዚህን ሐረጋት ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
እዚህ አካባቢ ገበያ አለ?
Is there a market near here?
እዚህ አካባቢ የሸቀጦች መደብር አለ?
Is there a supermarket near here?
እዚህ አካባቢ ሆስፒታል አለ?
Is there a hospital near here?
እዚህ አካባቢ የአውቶብስ መናኸሪያ አለ?
Is there a bus station near here?
ሁለተኛው ተናጋሪ አዎ፥ አለ ‘Yes, there is’ ካለ በኋላ ‘በጣብያው ጎዳና ላይ ነው የሚገኘው’ ‘It’s on Station Road’ ሲል አክሏል። ‘የሚገኘው’ ‘it’s on…’ ካለ በኋላ የጎዳናውን ስም ጨምሯል። በእንግሊዝኛ ቋንቋ ‘Street’ እና ‘Road’ ጎዳናን የምንገልፅባቸው የተለመዱ ቃላት ናቸው።
Yes, there is. It’s on Station Road.
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ለትብብሩ ‘አመሰግናለሁ’ ‘thanks!’ ብላለች። ሐረጉን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Thanks!
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ቦታዎች የት እንደሚገኙ ሲጠያየቁ በማዳመጥ እርስዎ ያሉትን ይፈትሹ።
ፒት ወደ ‘መናፈሻው ስፍራ’ ‘park’ መሄድ ይፈልጋል።
Is there a park near here?
Yes, there is. It’s on King George Street.
Thanks!
ክሌር ‘ሆቴል’ ‘hotel’ ትፈልጋለች።
Is there a hotel near here?
Yes, there is. It’s on East Street.
Thanks!
እሽ፤ አሁን ደግመን እንሞክር። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገራቱን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጣሉ።
Is there a restaurant near here?
Is there a restaurant near here?
Yes, there is.
Yes, there is.
It’s on Station Road.
It’s on Station Road.
Thanks!
Thanks!
በጣም ጥሩ! አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገራቱን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይናገሩ።
ምግብ ቤት በቅርብ አለ?
Is there a restaurant near here?
አዎ፥ አለ።
Yes, there is.
በጣብያው ጎዳና ላይ ነው።
It’s on Station Road.
አመሰግናለሁ።
Thanks!
በጣም ግሩም! እሽ አሁን በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ የተለያዩ ቦታዎች የት እንደሚገኙ በእንግሊዝኛ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል አውቀዋል። ለመጀመሪያዋ ተናጋሪ ምላሽ በመስጠት፥ እርስዎ ስለሚኖሩበት ከተማ ጥያቄዎችን በመሰንዘር ልምምድ ያድርጉ።
Is there a restaurant near here?
Thanks!
አሁን ሙሉውን ውይይት በድጋሚ ያዳምጡና መልስዎን እንደገና ይፈትሹ።
Sian
Is there a restaurant near here?
Phil
Yes, there is. It’s on Station Road.
Sian
Thanks!
በጣም ጥሩ። አሁን በእንግሊዝኛ በሚኖሩበት ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ስፍራዎች በተመለከተ መናገር እና ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ። የተማሩትን መለማምድን ያስታውሱ። ጓደኛ ይፈልጉና ስማችሁን መጠየቅና መናገርን ይለማመዱ። ለተጨማሪ የEssential English Conversation ዝግጅቶች በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ደህና ይሁኑ!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
Is there a... near here?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክከለኛውን መልስ ይምረጡ።
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክከለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
አንድ የመሸጫ መደብር ብቻ ነው ያለው።Question 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክከለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
በመልሱ ከጥያቄው ውስጥ አንድ ቃል ደግመናል።Question 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክከለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ከመንገዶች ጋር 'on'ን እንጠቀማለን።Question 3 of 3
Excellent! Great job! Bad luck! You scored:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
Is there a ______ near here?
______ እዚህ አካባቢ አለ እንዴ?
Yes, there is.
አዎ፥ አለ።
It’s on ______.
የሚገኘው በ ______ ላይ ነው።
Thanks!
አመሰግናለሁ።
a restaurant
ምግብ ቤት
a park
መናፈሻ
a hotel
ሆቴል